Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኢሳይያስ 54:14 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 በጽድቅ ትመሠረቻለሽ፤ የግፍ አገዛዝ ከአንቺ ይርቃል፤ የሚያስፈራሽ አይኖርም፤ ሽብር ከአንቺ ይርቃል፤ አጠገብሽም አይደርስም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 በጽድቅ ትታነጺያለሽ፤ ከግፍ ራቂ፥ አትፈሪምም፥ ድንጋጤም ወደ አንቺ አይቀርብም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 በፍትሕና በእውነት ላይ ትመሠረቺአለሽ፤ ግፍና ጭቈና ከአንቺ ይርቃል የሚያስፈራሽም የለም፤ ሽብርም ከአንቺ ይርቃል፤ ወደ አንቺም አይቀርብም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 እነሆ፥ በጽ​ድቅ ትታ​ነ​ጺ​ያ​ለሽ፤ ከግፍ ራቂ፤ አት​ፈ​ሪም፤ ድን​ጋ​ጤም ወደ አንቺ አይ​ቀ​ር​ብም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 በጽድቅ ትታነጺያለሽ፥ ከግፍ ራቂ፥ አትፈሪምም፥ ድንጋጤም ወደ አንቺ አትቀርብም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢሳይያስ 54:14
35 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ስትተኛ አትፈራም፤ ትተኛለህ እንቅልፍህም ጣፋጭ ይሆናል።


ፈራጆችሽን እንደ ጥንቱ፣ አማካሪዎችሽንም እንደ ቀድሞው እመልሳለሁ፤ ከዚያም የጽድቅ መዲና፣ የታመነች ከተማ ተብለሽ ትጠሪያለሽ።”


ጽዮን በፍትሕ፣ በንስሓ የሚመለሱ ነዋሪዎቿም በጽድቅ ይዋጃሉ።


በባቢሎን ንጉሥ ላይ ትሣለቃለህ፤ እንዲህም ትላለህ፤ ጨቋኙ እንዴት አበቃለት! አስገባሪነቱስ እንዴት አከተመ!


የሞዓባውያን ስደተኞች ከእናንተ ጋራ ይቈዩ፤ እናንተም ከአጥፊው መጠጊያ ሁኗቸው።” የጨቋኙ ፍጻሜ ይመጣል፤ ጥፋቱ ያከትማል፤ እብሪተኛም ከምድር ገጽ ይጠፋል።


እርሱ በሕዝቦች መካከል ይፈርዳል፤ የብዙ ሰዎችን አለመግባባት ያስወግዳል። እነርሱም ሰይፋቸውን ቀጥቅጠው ማረሻ፣ ጦራቸውንም ማጭድ ያደርጋሉ። ሕዝብ በሕዝብ ላይ ሰይፍ አያነሣም፤ ጦርነትንም ከእንግዲህ አይማሩም።


በእምነቱ የጸና ጻድቅ የሆነ ሕዝብ ይገባ ዘንድ፣ በሮቿን ክፈቱ።


የጽድቅ ፍሬ ሰላም፣ የጽድቅ ውጤትም ጸጥታና ለዘላለም ያለ ሥጋት ይሆናል።


የቀደመው መከራ ትዝ እያለህ፣ “ያ ዋና አለቃ የት አለ? ግብር ተቀባዩስ ወዴት ሄደ? የመጠበቂያ ማማ ኀላፊውስ የት አለ?” ትላለህ።


ስለ እኔም ሲናገሩ፣ ‘ጽድቅና ኀይል፣ በእግዚአብሔር ብቻ ነው’ ይላሉ።” በርሱ ላይ በቍጣ የተነሡ ሁሉ፣ ወደ እርሱ መጥተው ያፍራሉ።


አስጨናቂዎችሽ የራሳቸውን ሥጋ እንዲበሉ አደርጋቸዋለሁ፤ በወይን ጠጅ እንደሚሰከር ሁሉ፣ በገዛ ደማቸው ይሰክራሉ። ከዚያም የሰው ዘር ሁሉ፣ እኔ እግዚአብሔር አዳኝሽ፣ ታዳጊሽም የያዕቆብ ኀያል እንደ ሆንሁ ያውቃል።”


የፈጠረህን፣ ሰማያትን የዘረጋውን፣ ምድርን የመሠረተውን እግዚአብሔርን ረስተሃል፤ ሊያጠፋህ ከተዘጋጀው፣ ከጨቋኙ ቍጣ የተነሣ፣ በየቀኑ በሽብር ትኖራለህ፤ ታዲያ የጨቋኙ ቍጣ የት አለ?


ጽዮን ሆይ፤ ተነሺ፤ ተነሺ፤ ኀይልን ልበሺ፤ ቅድስቲቱ ከተማ፤ ኢየሩሳሌም ሆይ! የክብር ልብስሽን ልበሺ፤ ያልተገረዘ የረከሰም ከእንግዲህ ወደ አንቺ አይገባም።


“አይዞሽ አትፍሪ፤ ኀፍረት አይገጥምሽም፤ ውርደት ስለማይደርስብሽ አትሸማቀቂ፤ የወጣትነት ኀፍረትሽን ትረሺዋለሽ፤ የመበለትነት ስድብሽንም ከእንግዲህ አታስታውሺውም።


ከእንግዲህ በምድርሽ ሁከት፣ በጠረፎችሽም ጥፋትና መፈራረስ አይሰማም፤ ነገር ግን ቅጥሮችሽን ድነት፣ በሮችሽንም ምስጋና ብለሽ ትጠሪያቸዋለሽ።


ሕዝብሽም ሁሉ ጻድቃን ይሆናሉ፤ ምድሪቱንም ለዘላለም ይወርሳሉ፤ ለክብሬ መግለጫ ይሆኑ ዘንድ፣ የእጆቼ ሥራ፣ እኔ የተከልኋቸው ቍጥቋጦች ናቸው።


በእግዚአብሔር እጅግ ደስ ይለኛል፤ ነፍሴ በአምላኬ ሐሤት ታደርጋለች፤ ሙሽራ ራሱን እንደሚያሳምር፣ ሙሽራዪቱም በዕንቈቿ እንደምታጌጥ፣ የድነትን ልብስ አልብሶኛል፤ የጽድቅንም መጐናጸፊያ ደርቦልኛል።


ጽድቋ እንደ ማለዳ ወጋገን እስኪፈነጥቅ፣ ድነቷ እንደሚያንጸባርቅ ፋና እስኪታይ፣ ስለ ጽዮን ዝም አልልም፤ ስለ ኢየሩሳሌምም ጸጥ አልልም።


ምድያም ድል በተመታ ጊዜ እንደ ሆነው፣ የከበዳቸውን ቀንበር፣ በትከሻቸው ላይ የነበረውን በትር፣ የተጨቈኑበትንም ዘንግ ሰብረህላቸዋል።


ለመንግሥቱ ስፋት፣ ለሰላሙም ብዛት ፍጻሜ የለውም፤ ከአሁን ጀምሮ እስከ ዘላለም፣ መንግሥቱን በፍትሕና በጽድቅ ይመሠርታል፤ ደግፎ በመያዝም ያጸናዋል። በዳዊት ዙፋን ይቀመጣል፤ አገሩንም ሁሉ ይገዛል፤ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ቅናት ይህን ያደርጋል።


“ ‘ስለዚህ፤ አገልጋዬ ያዕቆብ ሆይ፤ አትፍራ፤ እስራኤል ሆይ፤ አትደንግጥ፤’ ይላል እግዚአብሔር። ‘አንተን ከሩቅ አገር፣ ዘርህንም ከተማረኩበት ምድር እታደጋለሁ፤ ያዕቆብ ተመልሶ በሰላምና በርጋታ ይቀመጣል፤ የሚያስፈራውም አይኖርም።


ልጆቻቸው እንደ ቀድሞው ይሆናሉ፤ ማኅበረ ሰቡም በፊቴ የጸና ይሆናል፤ የሚጨቍኗቸውን ሁሉ እቀጣለሁ።


የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ምርኳቸውን በመለስሁላቸው ጊዜ፣ እነርሱ በይሁዳ ምድርና በከተሞቿ፣ ‘አንተ የጽድቅ ማደሪያ ቅዱስ ተራራ ሆይ፤ እግዚአብሔር ይባርክህ!’ የሚል አነጋገር እንደ ገና ይጠቀማሉ።


ለራሳችሁ ጽድቅን ዝሩ፤ የጽኑ ፍቅርን ፍሬ ዕጨዱ፤ ዕዳሪውንም መሬት ዕረሱ፤ እርሱም መጥቶ፣ ጽድቅን በላያችሁ እስኪያዘንብ ድረስ፣ እግዚአብሔርን የምትፈልጉበት ጊዜ ነውና።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ወደ ጽዮን እመለሳለሁ፤ በኢየሩሳሌም እኖራለሁ፤ ኢየሩሳሌምም የእውነት ከተማ ትባላለች፤ የሰራዊት ጌታ የእግዚአብሔር ተራራም ቅዱስ ተራራ ይባላል።”


እኔ ግን ቤቴን ከዘራፊ ኀይሎች እጠብቃለሁ፤ ጨቋኝ ከእንግዲህ ሕዝቤን አይወርስም፤ አሁን ነቅቼ እጠብቃለሁና።


እኛ ግን ጽድቅ የሚኖርበትን አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር በተስፋ ቃሉ መሠረት እንጠባበቃለን።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች