Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -

ኢሳይያስ 54 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እስ​ራ​ኤ​ልን የወ​ደ​ደ​በት ፍቅር

1 አንቺ ያል​ወ​ለ​ድሽ መካን ሆይ፥ ደስ ይበ​ልሽ፤ አንቺ ያላ​ማ​ጥሽ ሆይ፥ እልል በዪ፤ ጩኺም፤ ባል ካላት ይልቅ ፈት የሆ​ነ​ቺቱ ልጆች በዝ​ተ​ዋ​ልና፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።

2 የድ​ን​ኳ​ን​ሽን ስፍራ አስፊ፤ መጋ​ረ​ጃ​ዎ​ች​ሽ​ንም ዘርጊ፤ አት​ቈ​ጥቢ፤ አው​ታ​ሮ​ች​ሽን አስ​ረ​ዝሚ፤ ካስ​ሞ​ች​ሽ​ንም ትከዪ።

3 እንደ ገና​ም​በ​ቀ​ኝና በግራ ተስ​ፋፊ፤ ዘርሽ አሕ​ዛ​ብን ይወ​ር​ሳ​ሉና፥ የፈ​ረ​ሱ​ት​ንም ከተ​ሞች መኖ​ሪያ ታደ​ር​ጊ​ያ​ለ​ሽና።

4 አታ​ፍ​ሪ​ምና አት​ፍሪ፤ አቷ​ረ​ጂ​ምና አት​ደ​ን​ግጪ፤ የዘ​ለ​ዓ​ለም እፍ​ረ​ት​ሽ​ንም ትረ​ሺ​ዋ​ለሽ፤ የመ​በ​ለ​ት​ነ​ት​ሽ​ንም ስድብ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ አታ​ስ​ቢም።

5 ፈጣ​ሪሽ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው፤ ስሙም የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም አም​ላክ ታዳ​ጊሽ ነው፤ እር​ሱም በም​ድር ሁሉ እን​ደ​ዚሁ ይጠ​ራል።

6 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ተተ​ወ​ችና እንደ ተበ​ሳ​ጨች፥ በል​ጅ​ነ​ቷም እንደ ተጠ​ላች ሴት የጠ​ራሽ አይ​ደ​ለም፥ ይላል አም​ላ​ክሽ።

7 ጥቂት ጊዜ ተው​ሁሽ፤ በታ​ላቅ ምሕ​ረ​ትም ይቅር እል​ሻ​ለሁ።

8 በጥ​ቂት ቍጣ ፊቴን ከአ​ንቺ ሰወ​ርሁ፤ በዘ​ለ​ዓ​ለም ቸር​ነት ይቅር እል​ሻ​ለሁ፥ ይላል ታዳ​ጊሽ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።

9 ከኖኅ ዘመን ውኃ ጀምሮ ይህ ለእኔ ምስ​ክር ነው፤ ቀድሞ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ምድ​ርን እን​ዳ​ል​ቈ​ጣት እንደ ማልሁ፥

10 ተራ​ሮ​ችን እን​ዳ​ል​ቀ​ሥ​ፋ​ቸው እን​ዳ​ላ​ፈ​ል​ሳ​ቸ​ውም፥ ኮረ​ብ​ቶ​ችም እን​ዳ​ይ​ነ​ዋ​ወጡ እንደ ማልሁ እን​ዲሁ ከእኔ ዘንድ ያለሽ ይቅ​ርታ አያ​ል​ቅም፤ የሰ​ላ​ምሽ ቃል ኪዳ​ንም አይ​ጠ​ፋም፤ መሓ​ሪሽ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህን ተና​ግ​ሮ​አ​ልና።

11 አንቺ የተ​ቸ​ገ​ርሽ የተ​ና​ወ​ጥሽ ያል​ተ​ጽ​ና​ና​ሽም፥ እነሆ፥ ድን​ጋ​ዮ​ች​ሽን የሚ​ያ​በሩ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ መሠ​ረ​ት​ሽ​ንም የሰ​ን​ፔር አደ​ር​ገ​ዋ​ለሁ።

12 ግን​ብ​ሽ​ንም በቀይ ዕንቍ፥ በሮ​ች​ሽ​ንም ቢረሌ በተ​ባለ ዕንቍ፥ ዳር​ቻ​ዎ​ች​ሽ​ንም በከ​በረ ዕንቍ እሠ​ራ​ለሁ።

13 ልጆ​ች​ሽም ሁሉ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ማሩ ይሆ​ናሉ፤ ልጆ​ች​ሽም በብዙ ሰላም ይኖ​ራሉ።

14 እነሆ፥ በጽ​ድቅ ትታ​ነ​ጺ​ያ​ለሽ፤ ከግፍ ራቂ፤ አት​ፈ​ሪም፤ ድን​ጋ​ጤም ወደ አንቺ አይ​ቀ​ር​ብም።

15 እነሆ፥ መጻ​ተ​ኞች በእኔ ወደ አንቺ ይመ​ጣሉ፤ በአ​ን​ቺም ይማ​ጸ​ናሉ።

16 እነሆ፥ ፍሙን በወ​ናፍ እን​ደ​ሚ​ያ​ናፋ፥ ለሥ​ራ​ውም መሣ​ሪያ እን​ደ​ሚ​ያ​ወጣ ብረት ሠሪ የፈ​ጠ​ር​ሁሽ አይ​ደ​ለም፤ እኔ ግን ለመ​ል​ካም ፈጠ​ር​ሁሽ እንጂ ለጥ​ፋት አይ​ደ​ለም።

17 በአ​ንቺ ላይ የተ​ሠራ መሣ​ሪያ ሁሉ እን​ዲ​ከ​ና​ወን አላ​ደ​ር​ግም፤ በአ​ንቺ ላይ ለፍ​ርድ የሚ​ነ​ሣ​ውን ድምፅ ሁሉ ታጠ​ፊ​ያ​ለሽ፤ ጠላ​ቶ​ች​ሽም ሁሉ ይፈ​ረ​ድ​ባ​ቸ​ዋል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ለሚ​ያ​ገ​ለ​ግሉ ርስት አላ​ቸው፤ ጻድ​ቃ​ኔም ትሆ​ኑ​ኛ​ላ​ችሁ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።

ተከተሉን:



ማስታወቂያዎች