Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




መክብብ 7:9 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 የሞኞች ቍጣ በዕቅፋቸው ውስጥ ስለ ሆነ፣ በመንፈስህ ለቍጣ አትቸኵል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 በነፍስህ ለቁጣ ችኩል አትሁን፥ ቁጣ በአላዋቂ ብብት ያርፋልና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ቊጣ የሰነፎች ቂም በቀል መወጫ ስለ ሆነ የቊጡነት ስሜትህን ተቈጣጠር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 በመ​ን​ፈ​ስህ ለቍጣ ችኩል አት​ሁን፥ ቍጣ በሰ​ነ​ፎች ብብት ያር​ፋ​ልና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 በነፍስህ ለቍጣ ችኩል አትሁን፥ ቍጣ በሰነፍ ብብት ያርፋልና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መክብብ 7:9
24 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ቃየንም ወንድሙን አቤልን፣ “እስኪ ና፤ ወደ መስኩ እንውጣ” አለው፤ በመስኩም ሳሉ፣ ቃየን ወንድሙን አቤልን አጠቃው፤ ገደለውም።


አቤሴሎም አምኖንን ክፉም ሆነ ደግ አንዳች ቃል አልተናገረውም፤ ምክንያቱም አምኖን እኅቱን ትዕማርን ስላስነወራት ጠልቶት ነበር።


አቤሴሎምም አገልጋዮቹን፣ “አምኖን የወይን ጠጅ ጠጥቶ መንፈሱ መለወጡን ተጠባበቁ፤ ከዚያም እኔ አምኖንን፣ ‘ምቱት’ ስላችሁ ግደሉት፤ ያዘዝኋችሁ እኔ ነኝ አትፍሩ፤ በርቱ፤ ጠንክሩ” ብሎ አዘዛቸው።


የዳዊት ወንድም የሳምዓ ልጅ ኢዮናዳብ ግን እንዲህ አለ፤ “የንጉሡን ልጆች በሙሉ እንደ ፈጇቸው አድርጎ ጌታዬ አያስብ፤ እኅቱን ትዕማርን በግድ ካስነወራት ጊዜ አንሥቶ አቤሴሎም ቈርጦ የተነሣበት ጕዳይ ስለ ሆነ፣ የሞተው አምኖን ብቻ ነው።


ከዚያም የእስራኤል ሰዎች ለይሁዳ ሰዎች፣ “እኛ እኮ ከንጉሡ ዐሥር እጅ ድርሻ አለን፤ ከዚህም በተጨማሪ በዳዊት ላይ ከእናንተ ይልቅ እኛ የበለጠ መብት አለን፤ ታዲያ እኛን የናቃችሁን ስለ ምንድን ነው? ንጉሣችን እንዲመለስ በመጀመሪያ የጠየቅነው እኛ አይደለንምን?” አሉ። ነገር ግን የይሁዳ ሰዎች የሰጡት መልስ የእስራኤል ሰዎች ከሰጡት መልስ ይልቅ እጅግ የከረረ ነበር።


ግልፍተኛ ሰው የቂል ተግባር ይፈጽማል፤ መሠሪም ሰው አይወደድም።


ታጋሽ ሰው ትልቅ ማስተዋል አለው፤ ግልፍተኛ ሰው ግን ቂልነትን ያሳያል።


ታጋሽ ሰው ከጦረኛ፣ ስሜቱን የሚገዛም ከተማን በጕልበቱ ከሚይዝ ይበልጣል።


ወደ ፍርድ አደባባይ በችኰላ አታውጣው፤ ባልንጀራህ ካሳፈረህ፣ ኋላ ምን ይውጥሃል?


አንተም፣ “ከእነዚህ ቀናት የቀድሞዎቹ ለምን ተሻሉ?” አትበል፤ እንዲህ ያሉትን ጥያቄዎች መጠየቅ ጠቢብነት አይደለምና።


አሁንም እግዚአብሔር ሆይ፤ ነፍሴን ውሰድ፤ ከመኖር መሞት ይሻለኛልና።”


ፀሓይ ስትወጣ፣ እግዚአብሔር የሚያቃጥል የምሥራቅ ነፋስ አመጣ፤ ፀሓዩም የዮናስን ራስ አቃጠለ፤ እርሱም ተዝለፈለፈ፤ መሞትም ፈልጎ፣ “ከመኖር መሞት ይሻለኛል” አለ።


እግዚአብሔር ግን ዮናስን፣ “በውኑ ስለ ቅሉ ልትቈጣ ይገባሃልን?” አለው። እርሱም፣ “በርግጥ እስከ ሞት ልቈጣ ይገባኛል” አለ።


ሄሮድያዳም በዚህ ቂም ይዛበት ልታስገድለው ፈለገች፤ ነገር ግን አልሆነላትም።


እርሷም ወጥታ እናቷን፣ “ምን ልለምነው?” አለቻት። እናቷም፣ “የመጥምቁ ዮሐንስን ራስ” አለቻት።


የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፤ ይህን አስተውሉ፤ ሰው ሁሉ ለመስማት የፈጠነ፣ ለመናገር የዘገየ፣ ለቍጣም የዘገየ ይሁን፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች