Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘዳግም 4:3 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 እግዚአብሔር በበኣል ፌጎር ላይ ምን እንዳደረገ በዐይናችሁ አይታችኋል፤ አምላካችሁ እግዚአብሔር ከመካከላችሁ በኣል ፌጎርን የተከተሉትን ሁሉ አጥፍቷቸዋል፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 የፌዖሩን ባዓልን የተከተሉትን ሰዎች ሁሉ ጌታ አምላካችሁ ከመካከላችሁ እንዳጠፋ፥ እግዚአብሔር በባዓል ፌዖር ያደረገውን ዐይኖቻችሁ አይተዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 በፔዖር ተራራ ላይ እግዚአብሔር ያደረገውን ሁሉ ራሳችሁ በዐይናችሁ አይታችኋል፤ ይኸውም በዚያ ተራራ ላይ ባዓል ተብሎ ለሚጠራው ጣዖት የሚሰግዱትን ሁሉ ደምስሶአል፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ብዔ​ል​ፌ​ጎ​ርን የተ​ከ​ተ​ለ​ውን ሰው ሁሉ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ና​ንተ ለይቶ አጥ​ፍ​ቶ​ታ​ልና አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በብ​ዔ​ል​ፌ​ጎር ያደ​ረ​ገ​ውን ዐይ​ኖ​ቻ​ችሁ አይ​ተ​ዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ብዔልፎጎርን የተከተሉትን ሰዎች ሁሉ አምላክህ እግዚአብሔር ከመካከላችሁ እንዳጠፋ፥ እግዚአብሔር በብዔልፎጎር ያደረገውን ዓይኖቻችሁ አይተዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘዳግም 4:3
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ለልጆቻቸው በምድረ በዳ እንዲህ አልኋቸው፤ “የአባቶቻችሁን ሥርዐት አትከተሉ፤ ወጋቸውን አትጠብቁ፤ ራሳችሁንም በጣዖቶቻቸው አታርክሱ።


“እስራኤልን ማግኘቴ፣ የወይንን ፍሬ በምድረ በዳ የማግኘት ያህል ነበር፤ አባቶቻችሁንም ማየቴ፣ የመጀመሪያውን የበለስ ፍሬ የማየት ያህል ነበር፤ ወደ በኣል ፌጎር በመጡ ጊዜ ግን፣ ለዚያ አሳፋሪ ጣዖት ራሳቸውን ለዩ፤ እንደ ወደዱትም ጣዖት የረከሱ ሆኑ።


ሙሴና ካህኑ አሮን በሲና ምድረ በዳ እስራኤላውያንን በቈጠሩ ጊዜ ከእነዚህ ከተቈጠሩት መካከል አንዳቸውም አልነበሩም፤


የበለዓምን ምክር ተቀብለው በፌጎር በተፈጸመው ድርጊት እስራኤላውያን ከእግዚአብሔር እንዲመለሱና የእግዚአብሔርም ሕዝብ እንዲቀሠፍ ያደረጉት እነርሱ ናቸው።


የእናንተ ዐይኖች ግን እግዚአብሔር ያደረጋቸውን ሥራዎች ሁሉ አይተዋል።


አምላካችሁን እግዚአብሔርን የተከተላችሁት እናንተ ሁላችሁ ግን ይኸው እስከ ዛሬ በሕይወት አላችሁ።


በፌጎር የተሠራው ኀጢአት አይበቃንምን? ምንም እንኳ በእግዚአብሔር ጉባኤ ላይ መቅሠፍት ቢወርድም፣ እስከ ዛሬዪቱ ዕለት ድረስ ራሳችንን ከዚያች ኀጢአት አላነጻንም።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች