Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዳንኤል 4:24 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 “ንጉሥ ሆይ፤ ትርጕሙ ይህ ነው፤ ልዑሉ በንጉሡ በጌታዬ ላይ ያወጣው ዐዋጅ ይህ ነው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 “ንጉሥ ሆይ! እነሆ፥ ትርጒሙ ይህ ነው፤ ልዑል እግዚአብሔር በአንተ በጌታዬ በንጉሡ ላይ እንዲፈጸም የወሰነው ነገር የሚከተለው ነው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 በጌታዬ በንጉሥ ላይ የወረደው የልዑሉ ትእዛዝ ነው፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዳንኤል 4:24
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እግዚአብሔር ለክፉ ሰዎች የወሰነው ዕድል ፈንታ፣ ከአምላክም ዘንድ የተመደበላቸው ቋሚ ቅርስ ይህ ነው።”


በመኳንንቱም ላይ መናቅን አዘነበባቸው፤ መውጫ መግቢያው በማይታወቅ በረሓ ውስጥም አንከራተታቸው።


ከዘላለም እስከ ዘላለም አጸናቸው፤ የማይሻርም ሕግ ደነገገላቸው።


የእግዚአብሔርን ሕግ ዐውጃለሁ፤ እርሱም እንዲህ አለኝ፤ “አንተ ልጄ ነህ፤ እኔ ዛሬ ወለድሁህ፤


በፍቅርና በታማኝነት ኀጢአት ይሰረያል፤ እግዚአብሔርን በመፍራት ሰው ከክፋት ይርቃል።


ፍቅርና ታማኝነት ንጉሥን ይጠብቁታል፤ በፍቅርም ዙፋኑ ይጸናል።


የክብርን ሁሉ ትዕቢት ሊያዋርድ፣ በምድር ከፍ ከፍ ያለውንም ሁሉ ዝቅ ሊያደርግ፣ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ወስኗል።


“ ‘ውሳኔው በመልእክተኞች ተገልጿል፤ ፍርዱም በቅዱሳኑ ተነግሯል፤ ይኸውም፣ ልዑል በሰዎች መንግሥታት ሁሉ ላይ እንደሚገዛና እነዚህንም መንግሥታት ለወደደው እንደሚሰጥ፣ ከሰዎችም የተናቁትን በላያቸው እንደሚሾም፣ ሕያዋን ሁሉ ያውቁ ዘንድ ነው።’


ከዚያም ብልጣሶር የተባለው ዳንኤል ለጥቂት ጊዜ በጣም ታወከ፤ ሐሳቡም አስደነገጠው። ንጉሡም፣ “ብልጣሶር ሆይ፤ ሕልሙም ሆነ ትርጕሙ አያስደንግጥህ” አለው። ብልጣሶርም እንዲህ ብሎ መለሰ፤ “ሕልሙ ለሚጠሉህ ይሁን፤ ትርጕሙም ለጠላቶችህ!


ልዑል አምላክ ያደረገልኝን ታምራዊ ምልክቶችንና ድንቅ ሥራዎች ስነግራችሁ እጅግ ደስ እያለኝ ነው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች