2 ሳሙኤል 14:9 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም9 ነገር ግን የቴቁሔዪቱም ሴት፣ “ንጉሥ ጌታዬ፣ በደሉ በእኔና በአባቴ ቤተ ሰብ ላይ ይሁን፤ ንጉሡና ዙፋኑ ከበደል የነጹ ይሁኑ” አለች። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)9 ነገር ግን የተቆዓዪቱም ሴት፥ “ንጉሥ ጌታዬ፥ በደሉ በእኔና በአባቴ ቤተሰብ ላይ ይሁን፤ ንጉሡና ዙፋኑ ከበደል የነጹ ይሁኑ” አለች። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም9 እርስዋም “ንጉሥ ሆይ! አንተ ስለምታደርገው ነገር ሁሉ እኔና ቤተሰቤ እንወቀስበት አንተና ዙፋንህ ግን ንጹሓን ሁኑ” አለችው። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)9 የቴቁሔዪቱም ሴት ንጉሡን፥ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፥ ኀጢአቱ በእኔና በአባቴ ቤት ላይ ይሁን፤ ንጉሡና ዙፋኑ ንጹሕ ይሁን” አለችው። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)9 የቴቁሔይቱም ሴት ንጉሡን፦ ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፥ ኃጢአቱ በእኔና በአባቴ ቤት ላይ ይሁን፥ ንጉሡና ዙፋኑ ንጹሕ ይሁን አለችው። ምዕራፉን ተመልከት |