Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




2 ሳሙኤል 14:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 የቴ​ቁ​ሔ​ዪ​ቱም ሴት ንጉ​ሡን፥ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፥ ኀጢ​አቱ በእ​ኔና በአ​ባቴ ቤት ላይ ይሁን፤ ንጉ​ሡና ዙፋኑ ንጹሕ ይሁን” አለ​ችው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ነገር ግን የቴቁሔዪቱም ሴት፣ “ንጉሥ ጌታዬ፣ በደሉ በእኔና በአባቴ ቤተ ሰብ ላይ ይሁን፤ ንጉሡና ዙፋኑ ከበደል የነጹ ይሁኑ” አለች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ነገር ግን የተቆዓዪቱም ሴት፥ “ንጉሥ ጌታዬ፥ በደሉ በእኔና በአባቴ ቤተሰብ ላይ ይሁን፤ ንጉሡና ዙፋኑ ከበደል የነጹ ይሁኑ” አለች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 እርስዋም “ንጉሥ ሆይ! አንተ ስለምታደርገው ነገር ሁሉ እኔና ቤተሰቤ እንወቀስበት አንተና ዙፋንህ ግን ንጹሓን ሁኑ” አለችው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 የቴቁሔይቱም ሴት ንጉሡን፦ ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፥ ኃጢአቱ በእኔና በአባቴ ቤት ላይ ይሁን፥ ንጉሡና ዙፋኑ ንጹሕ ይሁን አለችው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ሳሙኤል 14:9
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እና​ቱም አለ​ችው፥ “ልጄ ሆይ፥ መር​ገ​ምህ በእኔ ላይ ይሁን፥ ቃሌን ብቻ ስማኝ፤ ሂድና ያል​ሁ​ህን አም​ጣ​ልኝ።”


እኔ እዋ​ሳ​ለሁ፤ ከእጄ ትሻ​ዋ​ለህ፤ ወደ አንተ ባላ​መ​ጣው፥ በፊ​ት​ህም ባላ​ቆ​መው፥ በዘ​መ​ናት ሁሉ አን​ተን የበ​ደ​ል​ሁህ ልሁን።


ንጉ​ሡም፥ “የሚ​ና​ገ​ርሽ ማን ነው? አም​ጪ​ልኝ፤ ከዚ​ያም በኋላ ደግሞ አይ​ነ​ካ​ሽም” አለ።


ንጉ​ሡም ሴቲ​ቱን፥ “ወደ ቤትሽ በሰ​ላም ሂጂ፤ እኔም ስለ አንቺ አዝ​ዛ​ለሁ” አላት።


ደማ​ቸ​ውም በኢ​ዮ​አብ ራስና በዘሩ ራስ ላይ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይመ​ለስ፤ ለዳ​ዊት ግን ለዘ​ሩና ለቤቱ፥ ለዙ​ፋ​ኑም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰላም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይሁን።”


ምድ​ርን የሚ​ያ​ረ​ክ​ሳት ደም ነውና የም​ት​ኖ​ሩ​ባ​ትን ምድር በነ​ፍስ ግድያ አታ​ር​ክ​ሷት። ምድ​ሪ​ቱም በደም አፍ​ሳሹ ደም ካል​ሆነ በቀር ከፈ​ሰ​ሰ​ባት ደም አት​ነ​ጻም።


ሕዝቡም ሁሉ መልሰው “ደሙ በእኛና በልጆቻችን ላይ ይሁን፤” አሉ።


በእ​ግ​ሩም ላይ ወደ​ቀች፤ እን​ዲ​ህም አለች፥ “ጌታዬ ሆይ! ይህ ኀጢ​ኣት በእኔ ላይ ይሁን፤ እኔ ባሪ​ያህ በጆ​ሮህ ልና​ገር፥ የባ​ሪ​ያ​ህ​ንም ቃል አድ​ምጥ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች