1 ሳሙኤል 2:5 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም5 ጠግበው የነበሩ ለእንጀራ ሲሉ ተገዙ፤ ተርበው የነበሩ ግን እንጀራ ጠገቡ፤ መካኒቱ ሰባት ልጆች ወልዳለች፤ ብዙ ወንዶች ልጆች ወልዳ የነበረችው ግን መከነች። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)5 ጠግበው የነበሩ አጥተው ለእንጀራ ተገዙ፤ ተርበው የነበሩ ግን ከራብ ዐርፈዋል። መካኒቱ ሰባት ወለደች፥ ብዙ የወለደችው ግን ብቻዋን ቀረች። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም5 ጠግበው የነበሩ ተርበው ለምግብ ተገዝተዋል፤ ተርበው የነበሩ ግን ጠግበዋል፤ መኻኒቱ ሰባት ወለደች፤ የብዙዎች ልጆች እናት የነበረችው ብቻዋን ቀረች። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)5 እንጀራ ጠግበው የነበሩ ተራቡ፤ ተርበውም የነበሩ ጠገቡ፤ መካኒቱ ሰባት ወልዳለችና፥ ብዙም የወለደችው መውለድ አልቻለችም። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)5 ጠግበው የነበሩ እንጀራ አጡ፥ ተርበው የነበሩ ከራብ ዐርፈዋል፥ መካኒቱ ሰባት ወልዳለችና፥ ብዙም የወለደችው ደክማለች። ምዕራፉን ተመልከት |