Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 2:35 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

35 እንደ ልቤና እንደ አሳቤ የሚያገለግል የታመነ ካህን ለራሴ አስነሣለሁ፤ ቤቱን አጽንቼ አቆማለሁ፣ እርሱም በቀባሁት ፊት ለዘላለም ያገለግላል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

35 የታመነም ካህን ለእኔ አስነሣለሁ፤ እንደ ልቤና እንደ ሐሳቤም የሚያደርግ ይሆናል፤ እኔም የጸና ቤት እሠራለታለሁ፥ ዘመኑንም ሁሉ እኔ በቀባሁት ሰው ፊት ይሄዳል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

35 ለእኔም እንደ ልቤና እንደ ሐሳቤ የሚያደርግ አንድ ታማኝ ካህን አስነሣለሁ፤ ለእርሱም የጸና ዘር እመሠርትለታለሁ፤ እኔ በቀባሁትም ንጉሥ ፊት ይመላለሳል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

35 የታ​መነ ካህን ለእኔ አስ​ነ​ሣ​ለሁ፤ በል​ቤም፥ በነ​ፍ​ሴም እን​ዳለ እን​ዲሁ ያደ​ር​ጋል፤ እኔም የታ​መነ ቤት እሠ​ራ​ለ​ታ​ለሁ፤ ዘመ​ኑን ሁሉ እኔ በቀ​ባ​ሁት ሰው ፊት ይሄ​ዳል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

35 የታመነም ካህን ለእኔ አስነሣለሁ፥ በልቤም በነፍሴም እንዳለ እንዲሁ ያደርጋል፥ እኔም የታመነ ቤት እሠራለታለሁ፥ ዘመኑን ሁሉ እኔ በቀባሁት ሰው ፊት ይሄዳል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 2:35
28 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ለሕዝቤ ለእስራኤልም መሪዎች ከሾምሁለት ጊዜ አንሥቶ ያደረጉትን ዛሬ አያደርጉበትም፤ እንዲሁም ከጠላቶችህ ሁሉ እጠብቅሃለሁ። “ ‘እግዚአብሔር ራሱ ቤት እንደሚሠራልህ ይነግርሃል፤


“አቤቱ የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ ‘እኔ ለአንተ ቤት እሠራልሃለሁ’ ብለህ ይህን ለባሪያህ ገልጸህለታል። ስለዚህ ባሪያህ ይህችን ጸሎት ወደ አንተ ለማቅረብ በልቡ ደፈረ።


ካህኑ ሳዶቅና ነቢዩ ናታን በግዮን ቀብተው አንግሠውታል። ከዚያም ደስ ብሏቸው ወጥተዋል፤ ከተማዪቱም ይህንኑ አስተጋብታለች፤ እንግዲህ የሰማችሁት ድምፅ ይኸው ነው።


ነገር ግን ካህኑ ሳዶቅ፣ የዮዳሄ ልጅ በናያስ፣ ነቢዩ ናታን፣ ሳሚ፣ ሬሲና የዳዊት የክብር ዘበኞች ከአዶንያስ ጋራ አልተባበሩም።


ባሪያዬ ዳዊት እንዳደረገው ሁሉ አንተም ያዘዝሁህን ሁሉ ብትፈጽም፣ በመንገዴ ብትሄድ፣ ሥርዐቴንና ትእዛዜን በመጠበቅ ትክክል የሆነውን ነገር በፊቴ ብታደርግ፣ ከአንተ ጋራ እሆናለሁ፤ የዳዊትን ሥርወ መንግሥት እንዳጸናሁ፣ ለአንተም አጸናልሃለሁ፤ እስራኤልንም ለአንተ እሰጣለሁ።


ንጉሡም በኢዮአብ ቦታ የዮዳሄን ልጅ በናያስን በሰራዊቱ ላይ ሾመ፤ በአብያታርም ቦታ ካህኑን ሳዶቅን ተካ።


በዚያችም ዕለት በእግዚአብሔር ፊት በታላቅ ደስታ በሉ፤ ጠጡም። ከዚያም የዳዊት ልጅ ሰሎሞን ንጉሥ መሆኑን ለሁለተኛ ጊዜ በይፋ ዐወቁ፤ ገዥ እንዲሆንም በእግዚአብሔር ፊት ቀቡት፤ ሳዶቅንም ካህናቸው እንዲሆን ቀቡት።


እርሱ ላነገሠው ታላላቅ ድሎችን ይሰጣል፤ ጽኑ ፍቅሩንም ለቀባው፣ ለዳዊትና ለዘሩ ለዘላለም ይገልጣል።


የምድር ነገሥታት ተነሡ፤ ገዦችም በእግዚአብሔርና በመሲሑ ላይ ሊመክሩ ተሰበሰቡ፤


አዋላጆቹም እግዚአብሔርን በመፍራታቸው ቤተ ሰብ ሰጣቸው።


በእነርሱ ላይ አንድ እረኛ፣ ባሪያዬን ዳዊትን አቆማለሁ፤ እርሱም ያሰማራቸዋል፤ እረኛቸውም ይሆናል።


ለአምላኩ ክብር ቀንቶ ለእስራኤላውያን ስላስተሰረየላቸው፣ እርሱና ልጆቹ ዘላቂ የክህነት ቃል ኪዳን ይኖራቸዋል።”


ስለዚህ በሁሉም ነገር ወንድሞቹን መምሰል ተገባው፤ ይህንም ያደረገው መሓሪና ታማኝ ሊቀ ካህናት ሆኖ፣ እግዚአብሔርን ለማገልገልና ለሕዝቡ የኀጢአትን ስርየት ለማስገኘት ነው።


ጊብዓ በደረሱ ጊዜ የነቢያቱ ጉባኤ አገኙት፤ የእግዚአብሔር መንፈስ በኀይል ወረደበት፤ ከእነርሱም ጋራ ትንቢት ተናገረ።


ሳኦል ከሳሙኤል ተለይቶ ለመሄድ ፊቱን በመለሰ ጊዜ፣ እግዚአብሔር የሳኦልን ልብ ለወጠው፤ ምልክቱም ሁሉ በዚያ ዕለት ተፈጸመ።


እነሆ፤ ከፊታችሁ ቆሜአለሁ፤ በእግዚአብሔርና እርሱ በቀባው ፊት መስክሩብኝ፤ የማንን በሬ ወሰድሁ? የማንን አህያ ወሰድሁ? ማንን አታለልሁ? በማንስ ላይ ግፍ ሠራሁ? አይቶ እንዳላየ ለመሆንስ ከማን እጅ ጕቦ ተቀበልሁ? ከእነዚህ ሁሉ አንዱን እንኳ አድርጌ ከሆነ እመልስላችኋለሁ።”


ሳሙኤልም የዘይቱን ቀንድ ወስዶ በወንድሞቹ ፊት ቀባው። ከዚያ ቀን ጀምሮ የእግዚአብሔር መንፈስ በዳዊት ላይ በኀይል መጣ፤ ሳሙኤልም ወደ አርማቴም ሄደ።


ከዘሮችህም መካከል የተረፈው ማንኛውም ሰው፣ ለአንዲት ጥሬ ብርና ለቍራሽ እንጀራ ሲል በፊቱ ወድቆ ይሰግዳል፤ “የዕለት ጕርሴን እንዳገኝ እባክህ በማንኛውም የክህነት ሥራ ላይ መድበኝ” በማለት ይለምናል።’ ”


“ጌታዬ የእግዚአብሔርን ጦርነት ስለሚዋጋ እግዚአብሔርም ለጌታዬ ሥርወ መንግሥቱን በርግጥ ለዘላለም የሚያጸናለት በመሆኑ፣ እባክህ የእኔን የአገልጋይህን በደል ይቅር በል፤ በሕይወት ዘመንህም ሁሉ ክፋት አይገኝብህ።


ብላቴናው ሳሙኤል ከዔሊ በታች ሆኖ እግዚአብሔርን ያገለግል ነበር። በዚያም ዘመን የእግዚአብሔር ቃል ብርቅ ነበረ፤ ራእይም አይታይም ነበር።


ሳሙኤልም አንድ የሚጠባ የበግ ግልገል ወስዶ ሙሉ ለሙሉ የሚቃጠል መሥዋዕት በማድረግ ለእግዚአብሔር አቀረበው፤ ስለ እስራኤልም ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፤ እግዚአብሔርም መለሰለት።


ነገር ግን ልጆቹ የአባታቸውን ፈለግ አልተከተሉም፤ ተገቢ ያልሆነ ጥቅም ለማግኘት ሲሉ ከመንገዱ ወጡ፤ ጕቦ ተቀበሉ፤ ፍርድም አጣመሙ።


እነርሱም እንዲህ ሲሉ መለሱላቸው፤ “አዎን አለ፤ እነሆ፤ ከፊታችሁ ነው፤ ፈጠን በሉ፤ ሕዝቡ በማምለኪያው ኰረብታ ላይ መሥዋዕት ስለሚያቀርብ፣ ወደ ከተማችን ገና ዛሬ መምጣቱ ነው፤


ወደ ከተማዪቱም በገባችሁ ጊዜ፣ ለመብላት ወደ ማምለኪያው ኰረብታ ከመውጣቱ በፊት ታገኙታላችሁ። መሥዋዕቱን እርሱ መባረክ ስላለበት፣ እርሱ እስኪመጣ ድረስ ሕዝቡ መብላት አይጀምርም፤ ከዚያ በኋላ የተጋበዘው ሕዝብ ይበላል፤ አሁኑኑ ውጡ፤ ወዲያው ታገኙታላችሁ።”


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች