Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 85:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 እግዚአብሔር ሆይ! ዘለዓለማዊ ፍቅርህን አሳየን፤ አድነንም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 እግዚአብሔር ሆይ፤ ምሕረትህን አሳየን፤ ማዳንህን ለግሰን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 አቤቱ፥ ሕይወትን ልትሰጠን አትመለስምን? ሕዝብም በአንተ ደስ ይላቸዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 ትሰ​ማ​ኛ​ለ​ህና በመ​ከ​ራዬ ቀን ወደ አንተ እጮ​ኻ​ለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 85:7
5 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የምስጋና መሥዋዕት የሚያቀርብልኝ ያከብረኛል፤ መንገዴን ለሚከተል አዳኝነቴን አሳየዋለሁ።”


ዕድሜ እንዲጠግብ አደርገዋለሁ፤ አዳኝነቴንም አሳየዋለሁ።”


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ኤርምያስ ሆይ! ‘ይህች ምድር ሰዎችም ሆኑ እንስሶች የማይኖሩባት ባድማ ነች’ ያልከው አባባል ለጊዜው ትክክል ነው፤ የይሁዳ ከተሞችና የኢየሩሳሌም መንገዶች ምንም ሰዎች ወይም እንስሶች የማይታዩባት ባድማ ነች፤ አንድ ቀን ግን በዚህ ቦታ የተድላና የደስታ ድምፅ ይሰማል፤


በዚህ ቦታ የተድላና የደስታ፥ የሠርግ ዘፈን ድምፅ እንደገና ይሰማል፤ ከምርኮ ለተመለሱትም ቀድሞ የነበራቸውን ንብረታቸውን ስለምመልስላቸው የምስጋና መሥዋዕት ለማቅረብ ወደ ቤተ መቅደሴ በሚመጡበት ጊዜ፥ ‘የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ እርሱ ቸር ነውና፥ ፍቅሩም ዘለዓለማዊ ነውና’ እያሉ በከፍተኛ ድምፅ ይዘምራሉ። ይህን የተናገርኩ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።”


እኔ እራራላችኋለሁ፤ እርሱም እንዲራራላችሁና ወደ አገራችሁ እንዲመልሳችሁ አደርጋለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።’


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች