Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 71:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ተቃዋሚዎቼ ይፈሩ፤ ይጥፉም፤ ሊጐዱኝ የሚፈልጉ ይናቁ፤ ይዋረዱም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ባላንጣ የሆኑብኝ ይፈሩ፤ ይጥፉም፤ ሊጐዱኝ የሚፈልጉ፣ ንቀትንና ውርደትን ይከናነቡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ነፍሴን የሚቃወሙአት ይፈሩ ይጥፉም፥ ጉዳቴንም የሚፈልጉ እፍረትንና ኃሣርን ይልበሱ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ለድ​ሃና ለም​ስ​ኪን ይራ​ራል፥ የድ​ሆ​ች​ንም ነፍስ ያድ​ናል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 71:13
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በንጉሠ ነገሥቱ ግዛት በየከተማው አይሁድ በመኖሪያ ሰፈራቸው ሁሉ ጒዳት ሊያደርስባቸው በሚፈልግ በማንኛውም ሰው ላይ አደጋ ለመጣል በሚያስችላቸው ሁኔታ ተደራጁ፤ በየትኛውም ስፍራ የሚኖሩ ሕዝቦች ሁሉ ስለ ፈሩአቸው ማንም እነርሱን ለመቋቋም አልደፈረም።


ጠላቶቼ ውርደትን እንደ ልብስ ይልበሱ፤ ኀፍረትንም እንደ መጐናጸፊያ ይደርቡ።


ጠላቶቹ ኀፍረትን እንዲከናነቡ አደርጋቸዋለሁ፤ እርሱ ግን የሚያንጸባርቅ ዘውድ ይቀዳጃል።


በእኔ መከራ ተደስተው ትኲር ብለው በንቀት የሚመለከቱኝ ሁሉ ይፈሩ፤ ግራም ይጋቡ፤ በእኔ ላይ ራሳቸውን ከፍ ከፍ የሚያደርጉ ሁሉ ኀፍረትንና ውርደትን ይልበሱ።


እኔን ለመግደል የሚፈልጉ ሁሉ ኀፍረትና ውርደት ይድረስባቸው! በእኔ ላይ የሚያሤሩም ሁሉ ተዋርደው ወደ ኋላቸው ይመለሱ!


ጠላቶቼ ሁሉ ያፍራሉ፤ በድንገትም ተዋርደው ወደ ኋላቸው ይሸሻሉ።


እሰይ! እሰይ! እያሉ የሚያፌዙብኝ ሁሉ ዐፍረው ወደ ኋላቸው ይመለሱ።


ሊጐዱኝ የሚፈልጉ ስላፈሩና ግራ ስለ ተጋቡ አንደበቴ ቀኑን ሙሉ ስለ እውነተኛ ርዳታህ ይናገራል።


በአንተ ላይ የተቈጡ ሁሉ ተሸንፈው ያፍራሉ፤ አንተንም ለመጒዳት የሚነሡ ጠፍተው እንዳልነበሩ ይሆናሉ።


እግዚአብሔር ግን እንደ ጀግና ወታደር ከእኔ ጋር ነው፤ ስለዚህ አሳዳጆቼ በመደናቀፍ ኀይል አጥተው ይወድቃሉ። በሚወድቁበትም ጊዜ ክፉኛ ይዋረዳሉ፤ ውርደታቸውም ለረጅም ጊዜ ይታወሳል።


እንዲሁም እናንተ ጐልማሶች! ለሽማግሌዎች ታዘዙ፤ ሁላችሁም ትሕትናን እንደ ልብስ ለብሳችሁ አንዱ ሌላውን ያገልግል፤ “እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል ለትሑቶች ግን ጸጋን ይሰጣል” ተብሎ ተጽፎአልና።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች