Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 69:35 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

35 እርሱ ጽዮንን ያድናል፤ የይሁዳንም ከተሞች ያድሳል፤ ሕዝቡም በዚያ ይኖራሉ፤ ምድሪቱንም የራሳቸው ያደርጋሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

35 እግዚአብሔር ጽዮንን ያድናታልና፤ የይሁዳንም ከተሞች መልሶ ይሠራቸዋልና፤ ሕዝቡም በዚያ ይሰፍራል፤ ይወርሳታልም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

35 ሰማይና ምድር ባሕርም በእርሷም የሚንቀሳቀስ ሁሉ ያመሰግኑታል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 69:35
17 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ባሕርና በውስጡ ያሉት ሁሉ እልል ይበሉ! ማሳና በላይዋ የሚገኙ ሰብሎች ሁሉ ደስ ይበላቸው!


ለጽዮን ምሕረት የምታደርግላት ጊዜ ስለ ተቃረበና ጊዜውም አሁን ስለ ሆነ አንተ ትነሣለህ፤ ለእርስዋም ትራራለህ።


እግዚአብሔር ጽዮንን እንደገና በሚሠራበት ጊዜ በክብሩ ይገለጣል።


እግዚአብሔር ሆይ! ፍጡሮችህ ሁሉ ያመሰግኑሃል፤ ሕዝቦችህም ሁሉ ያወድሱሃል።


እኔ ሁልጊዜ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ፤ እርሱ የፈጠራቸው ሁሉ ቅዱስ ስሙን ለዘለዓለም ያወድሱ።


ከፍተኞች ሰማያት አመስግኑት፤ ከጠፈር በላይ ያላችሁ ውሃዎችም አመስግኑት።


አምላክ ሆይ! ጽዮንን ለመርዳት፥ የኢየሩሳሌምን ቅጥሮች ለመገንባት እባክህ ፈቃድህ ይሁን።


ከፍልስጥኤም ለሚመጡ መልእክተኞች የምንሰጠው መልስ ምንድን ነው? እግዚአብሔር ጽዮንን እንደገና መመሥረቱንና በሥቃይ ይኖሩ የነበሩ ሕዝቡ መጠጊያ አግኝተው በሰላም እንዲኖሩ ማድረጉን እንነግራቸዋለን።


ሰማያት ሆይ! እግዚአብሔር ሕዝቡን እስራኤልን በማዳን ክብሩን ገልጦአልና በደስታ ዘምሩ፤ ምድርም ከታች እልል በዪ፤ ተራራዎች፥ ጫካዎችና በውስጣቸው የምትገኙ ዛፎች ሁሉ የደስታ ድምፅ እያሰማችሁ ፈንድቁ።


የአገልጋዮቼን መልእክት አጸናለሁ፤ የነቢያቴንም ትንቢት እንዲፈጸም አደርጋለሁ፤፥ እነርሱም ኢየሩሳሌም፦ ‘የብዙ ሕዝብ መኖሪያ ትሆናለች፤ የይሁዳ ከተሞችም እንደገና ይሠራሉ፤ ፍርስራሾቻቸውም ይታደሳሉ’ ይላሉ።


ጽድቄን አቀርባለሁ፤ ሩቅም አይደለም፤ ማዳኔ አይዘገይም፤ ኢየሩሳሌምን አድናለሁ፤ ለእስራኤልም ክብሬን አጐናጽፋለሁ።”


“በጽዮን ተራራ ከጥፋት የሚያመልጡ ይገኛሉ፤ የጽዮን ተራራም የተቀደሰች ትሆናለች፤ የያዕቆብም ሕዝብ ተወስዶባቸው የነበረውን ንብረት መልሰው ይወስዳሉ።


ከዚህ በኋላ እነሆ በጉ በጽዮን ተራራ ላይ ቆሞ አየሁ፤ ከእርሱ ጋር የእርሱ ስምና የአባቱ ስም በግንባራቸው ላይ የተጻፈባቸው መቶ አርባ አራት ሺህ ሰዎች ነበሩ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች