Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 69:35 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

35 ሰማይና ምድር ባሕርም በእርሷም የሚንቀሳቀስ ሁሉ ያመሰግኑታል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

35 እግዚአብሔር ጽዮንን ያድናታልና፤ የይሁዳንም ከተሞች መልሶ ይሠራቸዋልና፤ ሕዝቡም በዚያ ይሰፍራል፤ ይወርሳታልም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

35 እርሱ ጽዮንን ያድናል፤ የይሁዳንም ከተሞች ያድሳል፤ ሕዝቡም በዚያ ይኖራሉ፤ ምድሪቱንም የራሳቸው ያደርጋሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 69:35
17 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የባርያዬን ቃል አጸናለሁ፤ የመልእክተኞቼንም ምክር እፈጽማለሁ፤ ኢየሩሳሌምን፦ የሰው መኖሪያ ትሆኛለሽ፥ የይሁዳንም ከተሞች፦ ትታነጻላችሁ ፍራሾቻችሁንም አቆማለሁ እላለሁ።


መሥዋዕትን ብትወድድስ በሰጠሁህ ነበር፥ የሚቃጠለውም መሥዋዕት ደስ አያሰኝህም።


ጽድቄን አቀርባለሁ፥ አይርቅም መድኃኒቴም አይዘገይም፤ ከጽዮን ለክብር እንዲሆን መድኃኒትን ለእስራኤል ሰጥቼአለሁ።


ነገር ግን በጽዮን ተራራ ላይ የሚያመልጡ ይኖራሉ፥ እርሱም የተቀደሰ ስፍራ ይሆናል፥ የያዕቆብም ቤት ሰዎች ርስታቸውን ይወርሳሉ።


ከዚያም አየሁ፤ እነሆም በጉ በጽዮን ተራራ ቆሞ ነበር፤ ከእርሱም ጋር ስሙና የአባቱ ስም በግምባራቸው የተጻፈላቸው መቶ አርባ አራት ሺህ ነበሩ።


ለሕዝቡም መልእክተኞች ምን ብሎ መልስ ይሰጣል? “ጌታ ጽዮንን መሥርቷል፥ ከሕዝቡም ችግረኞች በእርሷ ውስጥ መጠጊያን ያገኛሉ።”


አቤቱ፥ አሕዛብ ስምህን፥ ነገሥታትም ሁሉ ክብርህን ይፈራሉ፥


አንተ ግን፥ አቤቱ፥ ለዘለዓለም ትኖራለህ፥ መታሰቢያህም ለልጅ ልጅ ነው።


ባሕርና ሞላዋ በጩኽት ያስገምግሙ፤ በረሀ በእርሷም ያሉ ሁሉ ሐሤትን ያድርጉ።


አቤቱ፥ ሥራህ ሁሉ ያመሰግኑሃል፥ ቅዱሳንህም ይባርኩሃል።


አፌ የጌታን ምስጋና ይናገራል፥ ሥጋም ሁሉ ለዘለዓለም ዓለም የተቀደሰውን ስሙን ይባርክ።


ሰማየ ሰማያት፥ አመስግኑት፥ ከሰማያት በላይ ያላችሁም ውኃዎችም እንዲሁ።


ሰማያት ሆይ፥ ጌታ አድርጎታልና ዘምሩ፤ ጌታ ያዕቆብን ተቤዥቶአልና፥ በእስራኤልም ዘንድ ይከበራልና አንተ የምድር ጥልቅ ሆይ፥ ጩኽ፤ እናንተም ተራሮች አንተም ዱር በአንተም ያለ ዛፍ ሁሉ፥ እልል በሉ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች