Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 145:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 እግዚአብሔር ታላቅ ነው፤ ከፍተኛ ምስጋናም የሚገባው ነው፤ ታላቅነቱም ሰው ከሚያስተውለው በላይ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 እግዚአብሔር ታላቅ ነው፤ እጅግ ሊመሰገንም ይገባዋል፤ ታላቅነቱም አይመረመርም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ጌታ ታላቅ ነው እጅግም የተመሰገነ ነው፥ ታላቅነቱም የማይመረመር ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ማዳን በማ​ይ​ችሉ በአ​ለ​ቆ​ችና በሰው ልጆች አት​ታ​መኑ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 145:3
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እግዚአብሔር ታላቅ ነው፤ ከፍ ያለ ምስጋናም ይገባዋል፤ ከአማልክት ሁሉ ይበልጥ ሊፈራ ይገባዋል፤


እነዚህ ሁሉ እግዚአብሔር ከሚሠራቸው ነገሮች ጥቂቶቹ ናቸው፤ የምንሰማውም ሹክሹክታውን ብቻ ነው፤ የኀይሉን ነጐድጓድማ ማን ሊያስተውል ይችላል?”


የእግዚአብሔርን ታላቅነት መርምረን ልንደርስበት አንችልም፤ የዘመኑንም ልክ መመርመር አይቻልም።


እግዚአብሔር ሊታይ አይቻልም፤ ሥልጣኑም ታላቅ ነው፤ እርሱም ትክክለኛ ፈራጅ ነው።


እርሱ የማይቈጠረውን ተአምራት፦ የማይመረመረውን ታላቅ ነገር ያደርጋል።


እርሱ የሚያደርጋቸውን ድንቅ ነገሮች መርምረን ልናስተውል አንችልም፤ እርሱም የሚፈጽማቸውን ተአምራት ልንቈጥራቸው አንችልም።


የአንተ ዕውቀት እጅግ ጥልቅ ነው፤ እኔ ላስተውለው ከምችለው በላይ ነው።


አምላካችን ታላቅና ኀያል ነው፤ ለዕውቀቱም ወሰን የለውም።


እግዚአብሔር ታላቅ ስለ ሆነ በአምላካችን ከተማ፤ በተቀደሰ ተራራው ላይ ከፍ ያለ ምስጋና ሊቀርብለት ይገባዋል።


እግዚአብሔር ታላቅ ነው፤ ከፍ ያለ ምስጋናም ይገባዋል፤ ከአማልክትም ሁሉ ይበልጥ ሊፈራ ይገባዋል።


ከቶ አታውቅምን? ከቶስ አልሰማህምን? እግዚአብሔር የዘለዓለም አምላክ ነው፤ ዓለምን ሁሉ የፈጠረ እርሱ ነው፤ እርሱ ከቶ አይደክምም ወይም አይታክትም፤ ሐሳቡን መርምሮ ሊደርስበት የሚቻለው የለም።


የእግዚአብሔር ባለጸግነትና ጥበብ ዕውቀትም እንዴት ጥልቅ ነው! ፍርዱ የማይመረመር፥ መንገዱም የማይታወቅ ነው።


የእግዚአብሔርን አገልጋይ የሙሴን መዝሙርና የበጉን መዝሙር እንዲህ እያሉ ይዘምሩ ነበር፥ “ሁሉን የምትችል ጌታ አምላክ ሆይ! ሥራህ ታላቅና አስደናቂ ነው፤ የሕዝቦች ንጉሥ ሆይ! መንገድህ ትክክልና እውነት ነው፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች