Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 135:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 በዚያ ንጉሡን ፈርዖንንና አገልጋዮቹን ሁሉ ለመቅጣት ተአምራትንና ድንቅ ነገሮችን አደረገ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ግብጽ ሆይ፤ በፈርዖንና በአገልጋዮቹ ሁሉ ላይ፣ በመካከልሽ ታምራትንና ድንቅን ሰደደ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ግብጽ ሆይ፥ በመካከልሽ በፈርዖንና በባርያዎቹ ሁሉ ላይ ተኣምራትንና ድንቅን ሰደደ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ለጨ​ረ​ቃና ለከ​ዋ​ክ​ብት ሌሊ​ትን ያስ​ገ​ዛ​ቸው፤ ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 135:9
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በግብጽ ንጉሥ ላይ በባለሥልጣኖቹና በምድሩ በሚኖሩትም ሕዝብ ሁሉ ላይ ድንቅ ተአምራትን ገልጠህ አሳየህ። ይህንንም ያደረግኸው የቀድሞ አባቶቻችን እንዴት እንደሚጨቈኑ በማየትህ ነው፤ ይህንንም በማድረግህ እስከ ዛሬ ድረስ ዝናህ የገነነ ሆኖአል።


የግብጽን ንጉሥና ሠራዊቱን በቀይ ባሕር አሰጠመ፤ ፍቅሩ ዘለዓለማዊ ነው።


በግብጽ አገር በጾዓን ሜዳ የቀድሞ አባቶቻቸው እያዩ እግዚአብሔር በፊታቸው ተአምራትን አደረገ።


በግብጽና በቀይ ባሕር ድንቆችንና ተአምራትን በማድረግ ሕዝቡን አውጥቶ አርባ ዓመት የመራቸው ይህ ሙሴ ነበር።


ወይስ በፈተና፥ በተአምራትና በድንቅ ነገሮች፥ በጦርነት፥ በጸናች እጅና በተዘረጋ ክንድ፥ በሚያስፈራ ኀይል፥ በዐይናችሁ እያያችሁት እግዚአብሔር አምላካችሁ እናንተን ከግብጽ ምድር እንዳወጣችሁ ያለ አንድን ሕዝብ ከሌላ ሕዝብ መካከል ወስዶ የራሱ ሕዝብ ለማድረግ የሞከረ ሌላ አምላክ አለን?


ግብጻውያንን፥ ንጉሣቸውንና መኰንኖቻቸውን በብርቱ የሚጐዱ ታላላቅ ተአምራትን ማድረጉን በገዛ ዐይኖቻችን ዐይተናል፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች