Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 111:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 እግዚአብሔር ቸርና መሐሪ ነው፤ በአስደናቂ ሥራውም የገነነ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ድንቅ ሥራው ሲታወስ እንዲኖር አደረገ፤ እግዚአብሔር ቸር፣ ርኅሩኅም ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ለተአምራቱ መታሰቢያን አደረገ፥ ጌታ መሓሪና ርኅሩኅ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ለቅ​ኖች ብር​ሃን በጨ​ለማ ወጣ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሓ​ሪና ይቅር ባይ ነው፤ አም​ላ​ካ​ች​ንም ጻድቅ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 111:4
21 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ወደ እግዚአብሔር ብትመለሱ፥ እነዚያ ልጆቻችሁንና ዘመዶቻችሁን ማርከው የወሰዱ ሰዎች ለእነርሱ በመራራት ወደየመኖሪያ ስፍራቸው ተመልሰው እንዲመጡ ይፈቅዱላቸዋል፤ አምላካችሁ እግዚአብሔር ቸርና መሐሪ ስለ ሆነ እናንተ ወደ እርሱ ብትመለሱ እርሱ ፊቱን ከእናንተ አያዞርም።”


እግዚአብሔር መሐሪና ይቅር ባይ ነው። በቶሎ የማይቈጣና ለዘለዓለም ታማኝ ነው።


ምሕረትና ቸርነት፥ ቅንነትም ለሚያደርግ ለደግ ሰው በጨለማ ውስጥ ብርሃን ይወጣለታል።


እግዚአብሔር ቸርና መሐሪ ነው፤ ለቊጣ የዘገየና በዘለዓለማዊ ፍቅር የተሞላ ነው።


ሆኖም እግዚአብሔር ለሕዝቡ ምሕረትን አደረገ፤ ኃጢአታቸውን ይቅር አላቸው እንጂ አላጠፋቸውም። ብዙ ጊዜ ቊጣውን መለሰ፤ ብዙ ጊዜም መዓቱን ገታ።


እግዚአብሔር ሆይ! አንተ ግን መሐሪና ርኅሩኅ ለቊጣ የዘገየህ፥ የተትረፈረፈ ፍቅርና ታማኝነት ያለህ አምላክ ነህ።


ጌታ ሆይ! አንተ ለእኛ ቸርና መሐሪ ነህ፤ ወደ አንተ ለሚጸልዩትም ሁሉ ዘለዓለማዊ ፍቅርህን ታሳያቸዋለህ።


ለእኛ ስላደረጋቸው ድርጊቶች ሁሉ፥ ለእስራኤል ሕዝብ እንደ መሐሪነቱ ስላሳየው ከፍተኛ በጎ አመለካከት፥ ስለ ተትረፈረፈውም ዘለዓለማዊ ፍቅሩ የእግዚአብሔርን ቸርነት ምስጉን ድርጊቶቹን እዘረዝራለሁ።


እንግዲህ በምትኖሩበት ዘመን ሁሉ ይህን በዐይናችሁ ያያችሁትን ሁሉ እንዳትረሱና ከአእምሮአችሁ እንዳይጠፋ ተጠንቀቁ። ለልጆቻችሁና ለልጅ ልጆቻችሁም አስተምሩአቸው፤


የአምላካችን ጸጋ በኢየሱስ ክርስቶስ የእኛ ከሆነው እምነትና ፍቅር ጋር ተትረፍርፎ ተሰጠኝ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች