Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -

መዝሙር 111 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)


ሃሌ ሉያ።

1 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ፈራ፥ ትእ​ዛ​ዙ​ንም እጅግ የሚ​ወ​ድድ ሰው ብፁዕ ነው።

2 ዘሩ በም​ድር ላይ ኀያል ይሆ​ናል፤ የጻ​ድ​ቃን ትው​ል​ዶች ይባ​ረ​ካሉ።

3 ክብ​ርና ባለ​ጠ​ግ​ነት በቤቱ ነው፥ ጽድ​ቁም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይኖ​ራል።

4 ለቅ​ኖች ብር​ሃን በጨ​ለማ ወጣ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሓ​ሪና ይቅር ባይ ነው፤ አም​ላ​ካ​ች​ንም ጻድቅ ነው።

5 ርኅ​ሩኅ፥ ይቅር ባይና ቸር ሰው ነገ​ሩን በፍ​ርድ ይፈ​ጽ​ማል።

6 ለዘ​ለ​ዓ​ለም አይ​ታ​ወ​ክም፤ የጻ​ድቅ መታ​ሰ​ቢያ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይኖ​ራል።

7 ከክፉ ነገ​ርም አይ​ፈ​ራም፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለመ​ታ​መን ልቡ የጸና ነው።

8 በጠ​ላ​ቶቹ ላይ እስ​ኪ​ያይ ድረስ ልቡ ጽኑዕ ነው፥ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም አይ​ታ​ወ​ክም።

9 በተነ፥ ለች​ግ​ረ​ኞ​ችም ሰጠ፤ ጽድቁ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ዓለም ይኖ​ራል፤ ቀን​ዱም በክ​ብር ከፍ ከፍ ይላል።

10 ኀጢ​አ​ተ​ኛም አይቶ ይቈ​ጣል፥ ጥር​ሱ​ንም ያፋ​ጫል፥ ይቀ​ል​ጣ​ልም፤ የኃ​ጥ​ኣ​ንም ምኞት ትጠ​ፋ​ለች።

ተከተሉን:



ማስታወቂያዎች