Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ምሳሌ 5:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 ይህን ብታደርግ አስተዋይነት ይኖርሃል፤ ንግግርህም ዕውቀት እንዳለህ ይገልጣል፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 ይህም ልባምነትን ገንዘብ እንድታደርግ፣ ከንፈሮችህም ዕውቀትን እንዲጠብቁ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 ጥንቃቄን ትጠብቅ ዘንድ ከንፈሮችህም እውቀትን እንዲጠብቁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 መልካም ዐሳብን ትጠብቅ ዘንድ በከንፈሮቼ የማዝዝህን ዕወቅ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ምሳሌ 5:2
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አንተ የሰጠኸውን ሕግ ሁሉ መላልሼ አነባለሁ።


አንተ ከሰዎች ሁሉ ይልቅ እጅግ የተዋብክ ነህ፤ ንግግርህም ሞገስ የሞላበት ነው፤ እግዚአብሔር ለዘለዓለም ባርኮሃል።


ምንም እንኳ ማስተዋል ቢያዳግተኝ፥ አንደበቴ ስለ ትክክለኛ ፍርድህና ስለ አዳኝነትህ ቀኑን ሙሉ ይናገራል።


የደግ ሰው ንግግር ብዙ ሰዎችን ይጠቅማል፤ ሞኞች ግን ከማስተዋል ጒድለት የተነሣ ይሞታሉ።


የጠቢባን አንደበት ዕውቀትን ያፈልቃል። የሞኞች አፍ ግን ሞኝነትን ይለፈልፋል።


ዕውቀት የሚስፋፋው በብልኆች እንጂ በሞኞች አይደለም።


የጥበበኛ ሰው አእምሮ ንግግሩን ይቈጣጠራል፤ ከአፉም የሚወጣው ንግግር ትምህርትን ያስፋፋል።


ዕውቀት የተሞላበት ንግግር፥ ከወርቅና ከከበረ ዕንቊ ይበልጥ የተወደደ ነው።


ልጄ ሆይ! መልካም ጥበብንና አርቆ ማስተዋልን አጥብቀህ ያዝ፤ ከአንተም እንዲርቁ አታድርግ።


ሙሽራዬ ሆይ! ከከንፈሮችሽ የማር ወለላ ይፈስሳል፤ ከአንደበትሽም ማርና ወተት ይፈልቃል፤ የልብስሽም መዓዛ እንደ ሊባኖስ ሽቱ ነው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች