ዘኍል 28:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም14 ተገቢ ለሆነው የመጠጥ መባ ከእያንዳንዱ ኰርማ ጋር ሁለት ሊትር መጠጥ፥ ከአውራው በግ ጋር አንድ ተኩል ሊትር መጠጥ፥ ከእያንዳንዱም ጠቦት ጋር አንድ ሊትር የወይን ጠጅ አቅርቡ፤ በዓመቱ ሙሉ፥ ወር በገባ በመጀመሪያው ቀን ስለሚቀርበው የሚቃጠል መሥዋዕት የተሰጠው የሥርዓት መመሪያ ይኸው ነው። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም14 ከእያንዳንዱ ወይፈን ጋራ ለመጠጥ ቍርባን የሚሆን የሂን ግማሽ የወይን ጠጅ፣ ከአውራው በግ ጋራ የሂን አንድ ሦስተኛ፣ ከእያንዳንዱም የበግ ጠቦት ጋራ የኢን አንድ አራተኛ የወይን ጠጅ ይቅረብ፤ ይህም በየወሩ መባቻ ዓመቱን ሙሉ የሚቀርብ የሚቃጠል መሥዋዕት ነው። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)14 የመጠጥ ቁርባናቸውም ለአንድ ወይፈን የኢን ግማሽ፥ ለአውራው በግም የኢን ሢሶ፥ ለአንዱም ጠቦት የኢን አራተኛ እጅ የወይን ጠጅ ይሆናል፤ ይህ ለዓመቱ የወር መባቻ ሁሉ የሚቃጠል መሥዋዕት ነው። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)14 የመጠጥ ቍርባናቸውም ለአንድ ወይፈን የኢን ግማሽ፥ ለአውራው በግም የኢን ሲሦ፥ ለአንዱም ጠቦት የኢን አራተኛ እጅ የወይን ጠጅ ይሆናል፤ ይህ ለዓመቱ የወር መባቻ ሁሉ የሚቃጠል መሥዋዕት ነው። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)14 የመጠጥ ቍርባናቸውም ለአንድ ወይፈን የኢን ግማሽ፥ ለአውራው በግም የኢን ሢሶ፥ ለአንዱም ጠቦት የኢን አራተኛ እጅ የወይን ጠጅ ይሆናል፤ ይህ ለዓመቱ የወር መባቻ ሁሉ የሚቃጠል መሥዋዕት ነው። ምዕራፉን ተመልከት |