Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 21:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 የውሃ ጒድጓዱን የቈፈሩት፥ መሳፍንትና የሕዝብ አለቆች ናቸው፤ እነርሱም የውሃ ጒድጓዱን የቈፈሩት በበትረ መንግሥታቸውና በከዘራቸው ነው።” ከዚያም ምድረ በዳ ተነሥተው ወደ ማታና ተጓዙ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ልዑላን ለቈፈሩት፣ የሕዝብ አለቆች በበትረ መንግሥታቸውና በበትሮቻቸው ላጐደጐዱት፣ የውሃ ጕድጓድ ዘምሩለት።” ከዚህ በኋላ ከምድረ በዳው ወደ መቴና ሄዱ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 በበትረ መንግሥት በከዘራቸውም የሕዝብ አዛውንቶች የቈፈሩት፥ አለቆችም የማሱት ጉድጓድ። እነርሱም ከምድረ በዳም ወደ መቴና ተጓዙ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 “አለ​ቆች ቈፈ​ሩ​አት፥ በበ​ትረ መን​ግ​ሥት፥ በበ​ት​ራ​ቸ​ውም፥ የአ​ሕ​ዛብ ነገ​ሥ​ታት በመ​ን​ግ​ሥ​ታ​ቸ​ውና በግ​ዛ​ታ​ቸው አጐ​ደ​ጐ​ዱ​አት።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 በበትረ መንግሥት በበትራቸውም የሕዝብ አዛውንቶች ያጐደጐዱት፥ አለቆችም የቈፈሩት ጕድጓድ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 21:18
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የከተማይቱ ቅጽር እንደገና የተሠራው በዚህ ዐይነት ነበር፦ ሊቀ ካህናቱ ኤልያሺብና የእርሱ ሥራ ባልደረቦች የሆኑት ካህናት “የበጎች በር” ተብሎ የሚጠራውን ቅጽር በር እንደገና ሠርተው ለእግዚአብሔር የተለየ አደረጉት፤ በሮችንም አበጁለት፤ ቅጽሩንም “መቶ” ተብሎ እስከሚጠራው የመጠበቂያ ግንብና “ሐናንኤል” ተብሎ እስከሚጠራው ሌላ የመጠበቂያ ግንብ ድረስ ለእግዚአብሔር የተለየ አደረጉት።


የተቆዓ ከተማ ሰዎች ከዚያ ቀጥሎ ያለውን ክፍል ሠሩ፤ ነገር ግን የከተማይቱ ሹማምንት በተቈጣጣሪዎች የተመደበላቸውን የጒልበት ሥራ መሥራትን እምቢ አሉ።


እግዚአብሔር ዳኛችን፥ ሕግ ሰጪአችንና ንጉሣችን ነው፤ የሚያድነንም እርሱ ነው፤


በዚያን ጊዜ እስራኤላውያን ይህን መዝሙር ዘመሩ “ጒድጓድ ሆይ፥ ውሃ አፍልቅ፤ ለእርሱም ዘምሩለት


ከማታናም ወደ ናሕሊኤል፥ ከናሕሊኤልም ወደ ባሞት ዘለቁ፤


ሕግ በሙሴ በኩል ተሰጠ፤ ጸጋና እውነት ግን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል መጣ።


የእስራኤል ሕዝብ ርስት የሆነውን፥ ሙሴ የሰጠንን ሕግ ይጠብቃሉ።


አንተ ግን እዚህ እኔ አጠገብ ቁም፤ እኔም ሕግጋቴን፥ ትእዛዞቼንና ሥርዓቶቼን ሁሉ እሰጥሃለሁ፤ እኔ በምሰጣቸው ምድር እነዚህን ሕግጋቴን፥ ትእዛዞች ሥርዓቶቼን በመጠበቅ እንዲኖሩ ለሕዝቡ አስተምራቸው።’


ሕግን የሚሰጥና የሚፈርድ አንድ እግዚአብሔር ብቻ ነው፤ ሊያድንም ሊያጠፋም የሚችል እርሱ ብቻ ነው፤ ታዲያ፥ በሰው ላይ የምትፈርድ አንተ ማን ነህ?


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች