Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 21:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 በበትረ መንግሥት በከዘራቸውም የሕዝብ አዛውንቶች የቈፈሩት፥ አለቆችም የማሱት ጉድጓድ። እነርሱም ከምድረ በዳም ወደ መቴና ተጓዙ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ልዑላን ለቈፈሩት፣ የሕዝብ አለቆች በበትረ መንግሥታቸውና በበትሮቻቸው ላጐደጐዱት፣ የውሃ ጕድጓድ ዘምሩለት።” ከዚህ በኋላ ከምድረ በዳው ወደ መቴና ሄዱ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 የውሃ ጒድጓዱን የቈፈሩት፥ መሳፍንትና የሕዝብ አለቆች ናቸው፤ እነርሱም የውሃ ጒድጓዱን የቈፈሩት በበትረ መንግሥታቸውና በከዘራቸው ነው።” ከዚያም ምድረ በዳ ተነሥተው ወደ ማታና ተጓዙ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 “አለ​ቆች ቈፈ​ሩ​አት፥ በበ​ትረ መን​ግ​ሥት፥ በበ​ት​ራ​ቸ​ውም፥ የአ​ሕ​ዛብ ነገ​ሥ​ታት በመ​ን​ግ​ሥ​ታ​ቸ​ውና በግ​ዛ​ታ​ቸው አጐ​ደ​ጐ​ዱ​አት።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 በበትረ መንግሥት በበትራቸውም የሕዝብ አዛውንቶች ያጐደጐዱት፥ አለቆችም የቈፈሩት ጕድጓድ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 21:18
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ጌታ ፈራጃችን ነው፥ ጌታ ሕግን ሰጪያችን ነው፥ ጌታ ንጉሣችን ነው፤ እርሱ ያድነናል።


ሕግን የሚሰጥና የሚፈርድ አንድ ብቻ ነው፤ እርሱም ሊያድንና ሊያጠፋ የሚችል ነው፤ ነገር ግን በባልንጀራህ ላይ የምትፈርድ አንተ ማን ነህ?


ሕግ በሙሴ ተሰጥቶ ነበርና፤ ጸጋና እውነት ግን በኢየሱስ ክርስቶስ ሆነ።


ይህ ሙሴ የሰጠን ሕግ፥ የያዕቆብ ጉባኤ ርስት ነው።


አንተ ግን እዚህ እኔ አጠገብ ቁም፤ እኔ በምሰጣቸው ምድር እነዚህን በመጠበቅ እንዲኖሩ፥ ሕግጋቴን፥ ትእዛዞቼንና ሥርዓቶቼን ሁሉ እነግርሃለሁ።’


በአጠገባቸውም ቴቁአውያን አደሱ፤ መኳንንቶቻቸው ግን ለጌታቸው ሥራ አንገታቸውን አልሰጡም።


ሊቀ ካህኑ ኤልያሺብና ወንድሞቹ ካህናት ተነሥተው “የበግ በር” ሠሩ፤ ቀደሱት፥ በሩንም አቆሙ፤ እስከ “ሜአ ግንብ” እና እስከ “አሐናንኤል ግንብ” ድረስ ቀደሱት።


በዚያም ጊዜ እስራኤል ይህን መዝሙር ዘመረ፦ አንተ ምንጭ ሆይ! ፍለቅ፤ እናንተም ዘምሩለት፤


ከዚያም በኋላ ከመቴናም ወደ ነሃሊኤል፥ ከነሃሊኤልም ወደ ባሞት ተጓዙ፥


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች