Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኢያሱ 10:33 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

33 በዚህ ጊዜ የጌዜር ንጉሥ ሆራም ላኪሽን ለመርዳት መጥቶ ነበር፤ ነገር ግን ኢያሱ እርሱንና ሠራዊቱን ድል አደረገ፤ ከእነርሱም በሕይወት የተረፈ አንድ እንኳ አልነበረም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

33 በዚህ ጊዜ የጌዝር ንጉሥ ሆራም ለኪሶን ለመርዳት መጣ፤ ኢያሱ ግን አንድ እንኳ ሳያስተርፍ ንጉሡንና ሕዝቡን መታቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

33 በዚያን ጊዜም የጌዝር ንጉሥ ሆራም ለኪሶን ለመርዳት ወጣ፤ ኢያሱም አንድም እንኳ ሳይቀር እርሱንና ሕዝቡን መታ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

33 በዚያ ጊዜም የጋ​ዜር ንጉሥ ኤላም ላኪ​ስን ለመ​ር​ዳት ወጣ፤ ኢያ​ሱም አንድ ስንኳ ሳይ​ቀር በሰ​ይፍ ስለት እር​ሱ​ንና ሕዝ​ቡን መታ፤ የዳ​ነም፥ ያመ​ለ​ጠም የለም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

33 በዚያን ጊዜም የጌዝር ንጉሥ ሆራም ለኪሶን ለመርዳት ወጣ፥ ኢያሱም አንድ ስንኳ ሳይቀር እርሱንና ሕዝቡን መታ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢያሱ 10:33
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ዳዊትም እግዚአብሔር እንዳዘዘው አደረገ፤ ፍልስጥኤማውያንንም አሸነፈ፤ ከጌባዕ አንሥቶ እስከ ጌዜር ድረስም አባረራቸው።


ዘግየት ብሎም በጌዜር የሚኖሩ ፍልስጥኤማውያን ላይ ጦርነት ተደረገ፤ በዚያን ጊዜ የሑሻ ተወላጅ የሆነው ሲበካይ፥ ከራፋይም ወገን የነበረውን ሲፓይ ተብሎ የሚጠራውን ኀያል ሰው ገደለ፤ ፍልስጥኤማውያንም ተሸነፉ።


እነርሱም በኤፍሬም ኰረብቶች የምትገኘው የመማጠኛ ከተማ የሆነችው ሴኬም፥ ጌዜር፥


እግዚአብሔርም ጦርነቱ በተጀመረ በሁለተኛው ቀን ለእስራኤላውያን በላኪሽ ላይ ድልን ሰጣቸው፤ በሊብና ባደረጉትም ዐይነት በከተማይቱ ያገኙትን ሰው ሁሉ በሰይፍ ፈጁ፤


ቀጥሎም ኢያሱና ሠራዊቱ ከላኪሽ ወደ ዔግሎን ዘምተው ከበባ በማድረግ አደጋ ጣሉበት፤


እነዚህ ኤፍሬማውያን ግን በጌዜር የሚኖሩ ከነዓናውያንን አላስወጡም ነበር፤ ስለዚህም ከነዓናውያን እስከ አሁን ድረስ በኤፍሬማውያን መካከል ይኖራሉ፤ ሆኖም ለኤፍሬማውያን የጒልበት ሥራ ለመሥራት ይገደዳሉ።


ከዚያም በምዕራብ በኩል ወደሚገኙት ወደ ያፍሌጣውያን ይዞታ በመዝለቅ እስከ ታችኛው ቤትሖሮን ይደርሳል፤ ከዚያም ወደ ጌዜር ያልፍና መጨረሻው የሜድትራኒያን ባሕር ይሆናል።


ለእነርሱም የተሰጡት አራት ከተሞች ከመማጸኛ ከተሞች አንድዋ የሆነችው ሴኬምና በኮረብታማው በኤፍሬም አገር የሚገኙት የግጦሽ መሬቶችዋ፥ ጌዜር፥


የኤፍሬም ነገድም በጌዜር ይኖሩ የነበሩትን ከነዓናውያንን አላባረሩም ነበር፤ ስለዚህ ከነዓናውያን እዚያው ከእነርሱ ጋር ኗሪዎች ሆኑ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች