Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዮናስ 4:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 አሁንም ጌታ ሆይ! እባክህ ግደለኝ፤ ከመኖር ይልቅ መሞት ይሻለኛል።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 አሁንም እግዚአብሔር ሆይ፤ ነፍሴን ውሰድ፤ ከመኖር መሞት ይሻለኛልና።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 አሁንም፥ ጌታ ሆይ፥ ከሕይወት ሞት ይሻላልና፥ እባክህ ነፍሴን ከእኔ ውሰድ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 አሁ​ንም አቤቱ! ከሕ​ይ​ወት ሞት ይሻ​ለ​ኛ​ልና እባ​ክህ! ነፍ​ሴን ከእኔ ውሰድ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዮናስ 4:3
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ኤልያስ አንድ ቀን ሙሉ በበረሓ ተጓዘ፤ ከዚህ በኋላ ጒዞውን ቆም አድርጎ፥ በአንድ የክትክታ ዛፍ ጥላ ሥር ተቀመጠ፤ ሞቱንም በመመኘት “እግዚአብሔር ሆይ! አሁንስ ይብቃኝ፤ ከቀድሞ አባቶቼ አልበልጥምና ነፍሴን ውሰድ!” ሲል ጸለየ።


ዋጋው ውድ ከሆነ ከመልካም ሽቶ መልካም ስም ይሻላል፤ ከልደትም ቀን የሞት ቀን ይሻላል።


ቊጣ የሰነፎች ቂም በቀል መወጫ ስለ ሆነ የቊጡነት ስሜትህን ተቈጣጠር።


ከዚህም ክፉ ትውልድ የተረፉትና እኔ በበተንኳቸው ቦታ የሚኖሩትም ሕዝብ ከመኖር ይልቅ መሞትን ይመርጣሉ።”


እግዚአብሔርም “ይህን ያኽል ልትቈጣ ይገባሃልን?” አለው።


ፀሐይ ከወጣ በኋላ እግዚአብሔር የሚያቃጥል የምሥራቅ ነፋስ ላከ፤ የፀሐዩም ሐሩር ራሱን ስላቃጠለው ዮናስ ተዝለፈለፈ፤ ሞትንም በመመኘት “ከመኖር ይልቅ መሞት ይሻለኛል” አለ።


በዚህ ሁኔታ እንድሠቃይ ከምታደርገኝ ይልቅ መከራ እንዳላይ ብትራራልኝና አሁኑኑ ብትገድለኝ ይሻላል።”


እንዲህ በማለት ከሙሴ ጋር ተጣሉ፦ “በእግዚአብሔር ድንኳን ፊት ለፊት ከቀሩት እስራኤላውያን ወገኖቻችን ጋር ሞተን ቢሆን መልካም በሆነ ነበር።


እኔ ግን በእነዚህ መብቶች በአንዱም አልተጠቀምኩም፤ ይህንንም የጻፍኩት ይህ መብቴ ሳይከበርልኝ ለምን ቀረ? በማለት አይደለም። ሰው ትምክሕቴን ከንቱ ከሚያደርግብኝ ይልቅ ብሞት ይሻለኛል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች