Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኢዩኤል 1:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 ወንዞች ስለ ደረቁባቸው፥ የሜዳውም ሣር ሁሉ ስለ ተቃጠለባቸው፥ የዱር አራዊት እንኳ ወደ አንተ ይጮኻሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 የዱር አራዊት እንኳ ወደ አንተ አለኸለኹ፤ ወራጁ ውሃ ደርቋል፤ ያልተነካውንም መሰማሪያ እሳት በልቶታል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 ፈሳሹ ውኃ ደርቆአልና፥ እሳቱም የምድረ በዳውን ማሰማርያ በልቶአልና የምድር አራዊት ወደ አንተ አለኸለኹ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 ፈሳሹ ውኃ ደር​ቆ​አ​ልና፥ እሳ​ቱም የም​ድረ በዳ​ውን ውበት በል​ቶ​አ​ልና የም​ድር አራ​ዊት ወደ አንተ አን​ጋ​ጠጡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 ፈሳሹ ውኃ ደርቆአልና፥ እሳቱም የምድረ በዳውን ማሰማርያ በልቶአልና የምድር አራዊት ወደ አንተ አለኸለኹ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢዩኤል 1:20
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ዝናብ ጠፍቶ ድርቅ ከመሆኑ የተነሣ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ያ ወንዝ ደረቀ።


አክዓብ አብድዩን “ፈረሶችንና በቅሎዎችን ከሞት የምናድንበት በቂ ሣር እናገኝ እንደሆን በምድሪቱ ወደሚገኘው ምንጭና ወንዝ እስቲ ሂድና እይ፤ ምናልባት እንስሶቻችንን ከሞት ማዳን እንችል ይሆናል” አለው።


ልጆችዋ ምግብ አጥተው ሲቅበዘበዙ ወደ እኔም ሲጮኹ ለቁራ ምግብ የሚሰጣት ማነው?”


እግዚአብሔር የሚያዘጋጀውን ምግብ ሲያድኑ የአንበሳ ደቦሎች ያገሣሉ።


ሁሉም በተስፋ ወደ አንተ ይመለከታሉ፤ አንተም በሚያስፈልጋቸው ጊዜ ምግባቸውን ትሰጣቸዋለህ።


ለእንስሶች ምግብን ይሰጣል፤ ምግብ አጥተው የሚጮኹ የቊራ ጫጩቶችንም ይመግባል።


ዝናብ ከመጥፋቱ የተነሣ፥ ምድር ትደርቃለች፤ ገበሬዎችም ተስፋ በመቊረጥ፥ በሐዘን ራሳቸውን ይሸፍናሉ።


በጥንት ዘመን ከእኔና ከአንተ በፊት የተነሡ ነቢያት በብዙ ሕዝብና በታላላቅ መንግሥታት ላይ ጦርነት፥ ራብና ቸነፈር እንደሚመጣ ትንቢት ተናግረዋል፤


የግጦሽ ሣር በማጣት ከብቶች ያላዝናሉ፤ የበጎች መንጋ ሳይቀሩ ተርበው በብርቱ ሥቃይ ላይ ይገኛሉ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች