Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኢሳይያስ 9:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 እነሆ ሕፃን ተወልዶልናል! ወንድ ልጅም ተሰጥቶናል! እርሱም መሪ ይሆናል፤ ስሙም “ድንቅ መካር፥ ኀያል አምላክ፥ የዘለዓለም አባት፥ የሰላም አለቃ” ይባላል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ሕፃን ተወልዶልናል፤ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናል፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል። ስሙም፣ ድንቅ መካር፣ ኀያል አምላክ፣ የዘላለም አባት፣ የሰላም ልዑል ይባላል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 ለመንግሥቱ ስፋት፤ ለሰላሙም ብዛት ፍጻሜ የለውም፤ ከአሁን ጀምሮ እስከ ዘለዓለም፤ መንግሥቱን በፍትሕና በጽድቅ ይመሠርታል፤ ደግፎ በመያዝም ያጸናዋል። በዳዊት ዙፋን ይቀመጣል፤ አገሩንም ሁሉ ይገዛል፤ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፥ የዘለዓለም አባት ቅናት ይህን ያደርጋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 ሕፃን ተወ​ል​ዶ​ል​ና​ልና፥ ወንድ ልጅም ተሰ​ጥ​ቶ​ና​ልና፤ አለ​ቅ​ነ​ትም በጫ​ን​ቃው ላይ ይሆ​ናል፤ ስሙም ድንቅ መካር፥ ኀያል አም​ላክ፥ የዘ​ለ​ዓ​ለም አባት፥ የሰ​ላም አለቃ ተብሎ ይጠ​ራል፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፥ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፥ ስሙም ድንቅ መካር፥ ኃያል አምላክ፥ የዘላለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢሳይያስ 9:6
82 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ለስሜ መጠሪያ ቤት የሚሠራልኝም እርሱ ነው፤ የመንግሥቱንም ዙፋን ለዘለዓለም አጸናለሁ።


ቤትህና መንግሥትህ በፊቴ ይጠነክራል፤ ዙፋንህም ለዘለዓለም የጸና ይሆናል።’ ”


አምላክህ እግዚአብሔር ይመስገን! እርሱ አንተን መርጦ የእስራኤል ንጉሥ በማድረግ በአንተ መደሰቱን ገልጦልሃል፤ ለእስራኤል ያለውም ፍቅር ዘለዓለማዊ ስለ ሆነ ጽድቅና ፍትሕ ጸንቶ እንዲኖር ታደርግ ዘንድ የእስራኤል ንጉሥ አድርጎሃል።”


ኢዮአብ እነዚህን ሰዎች በመግደሉ በእርሱ ላይ የተፈጸመበት ቅጣት በእርሱና በዘሮቹ ላይ ለዘለዓለም ጸንቶ ይኑር፤ በዙፋኑ ላይ ለሚቀመጡት ለዳዊት ዘሮች ግን የእግዚአብሔር ሰላም ለዘለዓለም አይለያቸው።”


እኔን ግን እግዚአብሔር ይባርከኛል፤ የዳዊት መንግሥትም ለዘለዓለም ጸንቶ ይኖራል።”


“ቃል ኪዳንህንና ዘለዓለማዊ ፍቅርህን የምትጠብቅ፥ ታላቁ፥ ኀያሉና አስፈሪው አምላካችን ሆይ! በእኛ፥ በንጉሦቻችን፥ በመሪዎቻችን፥ በካህኖቻችን፥ በነቢዮቻችን፥ በቅድመ አያቶቻችን፥ እንዲሁም በሕዝብህ ሁሉ ላይ፥ ከአሦር ነገሥታት ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ፥ የደረሰውን መከራ ሁሉ አስብ።


በክብርና በግርማ የተሞላህ ኀያል ንጉሥ ሆይ፥ ሰይፍህን ታጠቅ።


አምላክ ሆይ! ዙፋንህ ለዘለዓለም እስከ ዘለዓለም የጸና ነው። በትረ መንግሥትህም የፍትሕ በትረ መንግሥት ነው።


አንተ መልካሙን ነገር ትወዳለህ፤ ክፉውን ነገር ትጠላለህ፤ ስለዚህ እግዚአብሔር አምላክህ መረጠህ፤ ከሌሎች ነገሥታትም ይበልጥ የደስታን ዘይት ቀባህ።


ኀያሉ እግዚአብሔር አምላክ ይናገራል፤ ከፀሐይ መውጫ እስከ መጥለቂያዋ ድረስ፥ በምድር ያለውን ሰው ሁሉ ይጠራል።


የንጉሡ ስም ለዘለዓለሙ ሲታወስ ይኑር፤ ዝናውም ፀሐይ በሚወጣበት ዘመን ሁሉ ይሰማ፤ ሕዝቦች ሁሉ በእርሱ የተባረኩ ይሁኑ፤ እርሱንም “የተባረከ ነው!” ይሉታል።


ተራራዎች ብልጽግናን፥ ኰረብቶችም የጽድቅ ፍሬን ለሕዝብ ያስገኙ።


በእርሱ ዘመን የጽድቅ ሥራ ይጠናከር፤ ጨረቃ ብርሃንዋን በምትሰጥበት ጊዜ ሁሉ ብልጽግና ይበርክት።


ፍቅርና እውነት ይተቃቀፋሉ፤ ጽድቅና ሰላም ይስማማሉ።


እግዚአብሔር ሆይ! ሰማያት ድንቅ ሥራዎችህን ያመስግኑ የሰማያዊው የቅዱሳን ጉባኤም ታማኝነትህን ከፍ ከፍ ያድርጉ።


ዓለም ከመፈጠርዋ አስቀድሞ፥ ከዘመናት በፊት ተሾምኩ።


ከእስራኤል ሕዝብ መካከል ከጥፋት የተረፉት ጥቂቶቹ ወደ ኀያል አምላካቸው በእውነት ይመለሳሉ።


ሕዝቡን የሚያስተዳድርበት የወገቡ መታጠቂያ እውነት፥ የጐኑም መቀነት ታማኝነት ይሆናል።


በዚያን ጊዜ አንድ መንግሥት በዘለዓለማዊ ፍቅር ይመሠረታል፤ በዙፋኑም ላይ ከዳዊት ዘር አንድ ታማኝ የሆነ፥ ፍትሕን የሚፈልግና ትክክለኛውን ነገር ለማድረግ ፈጣን የሆነ ንጉሥ ይቀመጥበታል።


አምላክ ሆይ፥ ሰላምን አሰፈንክልን፤ ሥራችንን ሁሉ የፈጸምክልን አንተ ነህ።


ጌታ ሆይ! በእምነታቸው ለጸኑ ሰዎች ፍጹም ሰላምን ትሰጣቸዋለህ።


የዚህ ሁሉ ጥበብ መገኛ የሠራዊት አምላክ ነው፤ እርሱ አስደናቂ መካሪ ጥበቡም ፍጹም ነው።


በጽድቅ የሚያስተዳድር ንጉሥ የሚነሣበት ጊዜ ይመጣል፤ ሹማምንቱም በትክክል ይፈርዳሉ።


ይህ ሁሉ እንዲፈጸም የሠራዊት አምላክ ቅናት ስለ ወሰነ ከኢየሩሳሌምና ከጽዮን ኰረብታ ከጥፋት የሚተርፉ ይኖራሉ።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ይሁን እንጂ በሕማም አደቀው ዘንድ የእኔ ፈቃድ ነበር፤ ሕይወቱን የበደል መሥዋዕት አድርጎ በሚያቀርብበት ጊዜ ዘመኑ ተራዝሞ ብዙ ትውልድ ያያል፤ በእርሱም አማካይነት የእኔ ፈቃድ ይፈጸማል።


አገልጋዬ በደረቅ ምድር ላይ እንደሚወጣ ሥርና እንደ ቡቃያ አድጓል፤ እንመለከተው ዘንድ ውበት ወይም ግርማ የለውም፤ እርሱን እንወደው ዘንድ ከመልኩ አንዳች እንኳ የሚስብ ደም ግባት የለውም።


እርሱ ግን ተወግቶ የቈሰለው ስለ መተላለፋችን ነው፤ የደቀቀውም ስለ በደላችን ነው፤ እኛ የዳንነው እርሱ በተቀበለው ቅጣት ነው፤ በእርሱም ቊስል እኛ ተፈወስን።


አብርሃም ባያውቀን፥ እስራኤል ባይቀበለንም እንኳ አንተ አባታችን ነህ፤ አምላክ ሆይ! ስምህ ከጥንት እንደ ሆነ ሁሉ አንተ አባታችን ነህ፤ አንተ ታዳጊአችን ነህ።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ሀብትዋን እንደ ወንዝ ውሃ አበዛዋለሁ፤ የሕዝቦችንም ሀብት እንደ ወንዝ ጅረት አደርገዋለሁ፤ በክንድዋም ተይዛችሁ ትጠባላችሁ፤ በጭንዋም ላይ አድርጋ ትንከባከባችኋለች።


እንግዲህ እግዚአብሔር ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፤ እነሆ ድንግል ትፀንሳለች፤ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፤ ስሙንም ‘ዐማኑኤል’ ብላ ትጠራዋለች፤


እነሆ፥ ልጆቼና እኔ በጽዮን ተራራ ላይ ከሚኖረው ከሠራዊት አምላክ ለእስራኤል ሕዝብ የተሰጠን የማስጠንቀቂያ ምልክት ነን።


እናንተ እምነት የጐደላችሁ ሕዝብ፥ እስከ መቼ ታመነታላችሁ? እኔ እግዚአብሔር በምድር ላይ አዲስ ነገርን ፈጥሬአለሁ፤ ይኸውም ሴት ለወንድ ትከላከላለች። ልዩ የሆነ አዲስ ነገር ፈጥሬአለሁ።”


በእነዚያም ነገሥታት ዘመን የሰማይ አምላክ ፈጽሞ የማይፈርስና ግዛቱም በሌላ ሕዝብ የማይደፈር መንግሥትን ይመሠርታል፤ ይህ መንግሥት ሌሎችን መንግሥታት እስከ መጨረሻው ያጠፋቸዋል፤ እርሱ ግን ለዘለዓለም ጸንቶ ይኖራል፤


በልዩ ልዩ አገር የሚኖሩ ሕዝቦችና ልዩ ልዩ ቋንቋ የሚናገሩ ነገዶች ያገለግሉት ዘንድ ሥልጣን፥ ክብርና ንጉሥነት ተሰጠው፤ ግዛቱም የማይጠፋ ዘለዓለማዊ ነው፤ ለመንግሥቱም ፍጻሜ የለውም።


አዲሱ ቤተ መቅደስ ከፊተኛው ይበልጥ የተዋበ ይሆናል፤ እኔም በዚያ ለሕዝቤ የተሟላ ሰላምን እሰጣለሁ፤” የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ይህን ተናግሮአል።


የዳዊትና የአብርሃም ዘር የሆነው የኢየሱስ ክርስቶስ የትውልድ ሐረግ ይህ ነው፦


“እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፤ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፤ ስሙም ‘ዐማኑኤል’ ተብሎ ይጠራል።” ዐማኑኤል ማለትም “እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው” ማለት ነው።


አባቴ ሁሉን ነገር ሰጥቶኛል፤ ከአብ በቀር ወልድን የሚያውቅ ማንም የለም። እንዲሁም ከወልድ በቀር አብን የሚያውቅ የለም፤ ማንም ወልድ ካልገለጠለት በቀር አብን ሊያውቅ አይችልም።


ኢየሱስ ወደ እነርሱ ቀረበና እንዲህ አላቸው፤ “ሥልጣን ሁሉ በሰማይና በምድር ተሰጥቶኛል፤


መልአኩም እንዲህ ሲል መለሰ፦ “መንፈስ ቅዱስ በአንቺ ላይ ይመጣል፤ የልዑል እግዚአብሔርም ኀይል በአንቺ ላይ ይሆናል፤ ስለዚህ ከአንቺ የሚወለደው ሕፃን ቅዱስ ነው፤ የእግዚአብሔርም ልጅ ይባላል።


እነሆ! ዛሬ በዳዊት ከተማ አዳኝ ተወልዶላችኋል፤ እርሱም ጌታ ክርስቶስ ነው።


“በሰማይ ለእግዚአብሔር ክብር ይሁን! በምድርም እግዚአብሔር ለሚወዳቸው ሰዎች ሁሉ ሰላም ይሁን!” ይሉ ነበር።


ከጠላቶቻችሁ ማንም ሊቋቋመው ወይም ሊቃወመው የማይችለውን አንደበትና ጥበብ እኔ እሰጣችኋለሁ።


ቃልም ሥጋ ሆነ፤ ጸጋንና እውነትንም ተመልቶ በመካከላችን ኖረ፤ የአባቱ አንድያ ልጅ በአባቱ ዘንድ እንዳለው ያለውን ክብሩን አይተናል።


ከእርሱ የጸጋ ሙላት እኛ ሁላችን በጸጋ ላይ ጸጋን ተቀብለናል።


“ሰላምን እተውላችኋለሁ፤ ሰላሜንም እሰጣችኋለሁ፤ እኔ የምሰጣችሁ ሰላም ዓለም እንደሚሰጠው ዐይነት አይደለም፤ ልባችሁ አይጨነቅ፤ ደግሞም አይፍራ።


እግዚአብሔር ለእስራኤል ሕዝብ ቃሉን መላኩ የታወቀ ነው፤ በሁሉ ጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት ሰላምን እየሰበከ የመጣውም ለእነርሱ ነው።


መንፈስ ቅዱስ እናንተን ኤጲስ ቆጶሳት አድርጎ ሾሞአችኋል፤ እንግዲህ ለራሳችሁና ለመንጋው ተጠንቀቁ፤ እግዚአብሔር በገዛ ልጁ ደም የዋጃትን ቤተ ክርስቲያን ጠብቁ።


እግዚአብሔር ለአንድ ልጁ ሳይራራ ስለ እኛ አሳልፎ ከሰጠው እንዴት ከልጁ ጋር ሁሉን ነገር በነጻ አይሰጠንም?


እነርሱ በትውልዳቸው ከነገድ አባቶች የመጡ ናቸው፤ ክርስቶስም በሥጋ የመጣው ከእነርሱ ዘር ነው፤ እርሱ ከሁሉ በላይ ነው፤ ለዘለዓለምም የተባረከ አምላክ ነው፤ አሜን!


እናንተን ግን እግዚአብሔር ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ኅብረት እንዲኖራችሁ አደረገ፤ ስለዚህ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስን ጥበባችን፥ ጽድቃችን፥ ቅድስናችንና ቤዛችን እንዲሆን አደረገው።


እግዚአብሔር ጠላቶቹን ሁሉ በሥልጣኑ ሥር እስኪያደርግለት ድረስ ክርስቶስ መንገሥ ይገባዋል።


ይህም እግዚአብሔር በክርስቶስ የዓለምን ሰዎች ሁሉ ከራሱ ጋር አስታረቀ ማለት ነው፤ በደላቸውንም አልቈጠረባቸውም፤ ለእኛም ሰውን ከጌታ ጋር የምናስታርቅበትን ቃል ሰጠን።


እግዚአብሔር አምላካችሁ ከባዕዳን አማልክት ሁሉና ከኀይላትም ሁሉ በላይ ታላቅና ብርቱ ስለ ሆነ በፍርሃት መከበር ይገባዋል። እርሱ በፍርድ አያዳላም፤ ጉቦም አይቀበልም።


የጥበብና የዕውቀት ሀብት ተሰውሮ የሚገኘው በክርስቶስ ዘንድ ነው።


የሃይማኖታችን ምሥጢር ያለ ጥርጥር ታላቅ ነው፤ እርሱም እግዚአብሔር፦ “ሰው ሆኖ ተገለጠ፤ እውነተኛነቱ በመንፈስ ታወቀ፥ ለመላእክት ታየ፥ ለሕዝቦች ሁሉ ተሰበከ፥ በዓለም ያሉ ሰዎች አመኑበት፥ በክብር ወደ ሰማይ ዐረገ” የሚል ነው።


በዚህ ዐይነት የተባረከውን ተስፋችንን እንዲሁም የታላቁ አምላካችንን፥ የአዳኛችንን የኢየሱስ ክርስቶስን በክብር መገለጥ እንጠባበቃለን።


ስለ ልጁ ግን፥ “አምላክ ሆይ! ዙፋንህ ለዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ይኖራል፤ መንግሥትህንም በትክክል ታስተዳድራለህ፤


ታላቁን የበጎች እረኛ ጌታችንን ኢየሱስን በዘለዓለማዊ ቃል ኪዳን ደም ከሞት ያስነሣው የሰላም አምላክ


የእግዚአብሔር ልጅ እንደ መጣና እውነተኛውን አምላክ እንድናውቅ አስተዋይ ልቡና እንደ ሰጠን እናውቃለን በልጁም በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ከእርሱ ከእውነተኛው አምላክ ጋር ኅብረት አለን። ኢየሱስ ክርስቶስ እውነተኛው አምላክና የዘለዓለም ሕይወት ነው።


በልብሱና በጭኑ ላይ “የነገሥታት ንጉሥ፥ የጌቶች ጌታ” የሚል ስም ተጽፎአል።


መልአኩም “ስሜን ለማወቅ የፈለግኸው ለምንድን ነው? ስሜ ድንቅ ነው” ሲል መለሰለት።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች