Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




2 ነገሥት 5:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 አንድ ቀን እመቤትዋን፥ “ጌታዬ ንዕማን በሰማርያ ወደሚገኘው ነቢይ ቢሄድ መልካም ይመስለኛል! ነቢዩ ከዚህ የቆዳ በሽታው ሊያነጻው ይችላል!” አለቻት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 እመቤቷንም፣ “ጌታዬ በሰማርያ ያለውን ነቢይ ሄዶ ቢያገኘው እኮ ከዚህ ቈዳ በሽታው ይፈውሰው ነበር” አለቻት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 አንድ ቀን እመቤትዋን፥ “ጌታዬ ንዕማን በሰማርያ ወደሚገኘው ነቢይ ቢሄድ መልካም ይመስለኛል! ነቢዩ ከዚህ የቆዳ በሽታው ሊያነጻው ይችላል!” አለቻት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 እመ​ቤ​ቷ​ንም፥ “ጌታዬ በሰ​ማ​ርያ ወደ​ሚ​ኖ​ረው ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው ወደ ነቢዩ ይሄድ ዘንድ በተ​ገ​ባው ነበር፤ ከለ​ም​ጹም በፈ​ወ​ሰው ነበር” አለ​ቻት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 እመቤትዋንም “ጌታዬ በሰማርያ ካለው ከነቢዩ ፊት ቢደርስ ኖሮ ከለምጹ በፈወሰው ነበር፤” አለቻት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ነገሥት 5:3
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሶርያውያን በእስራኤላውያን ላይ ወረራ በፈጸሙበት በአንድ ወቅት፥ አንዲት ትንሽ እስራኤላዊት ልጃገረድ ማርከው ወስደው ነበር፤ እርስዋም ለንዕማን ሚስት፥ ገረድ ሆና ትኖር ነበር።


ንዕማንም ይህን በሰማ ጊዜ ወደ ንጉሡ ቀርቦ ልጃገረዲቱ ያለችውን ሁሉ ነገረው፤


ነቢዩ ኤልሳዕም የሆነውን ነገር ሁሉ በሰማ ጊዜ ወደ ንጉሡ መልእክት ልኮ “ስለምን ልብስህን ቀደድክ? ሰውየውን ወደ እኔ ላከው፤ እኔም በእስራኤል ነቢይ መኖሩን አሳየዋለሁ!” አለው።


ሙሴም “አንተ ስለ እኔ ትቈረቈራለህን? እኔስ እግዚአብሔር በሕዝቡ ሁሉ ላይ መንፈሱን ቢያወርድና ሁሉም ድምፃቸውን ከፍ አድርገው እንደ ነቢያት ትንቢት ቢናገሩ ደስታዬ ነው!” አለው።


እነሆ፥ ዕውሮች ያያሉ፤ አንካሶች ቀጥ ብለው ይሄዳሉ፤ ለምጻሞች ይነጻሉ፤ ደንቆሮዎች ይሰማሉ፤ ሙታን ይነሣሉ፤ ለድኾችም ወንጌል ይሰበካል፤


ጳውሎስም “በአጭር ጊዜም ይሁን በረጅም ጊዜ አንተ ብቻ ሳትሆን ዛሬ ንግግሬን የሰሙ ሁሉ ከዚህ ከእስራቴ በቀር እንደ እኔ እንዲሆኑ እግዚአብሔርን እለምናለሁ!” አለ።


አሁንማ የሚያስፈልጋችሁን ነገር ሁሉ አግኝታችኋል፤ አሁንማ ሀብታሞች ሆናችኋል፤ ከእኛም ተለይታችሁ ነግሣችኋል፤ በእርግጥ ብትነግሡማ ኖሮ፥ እኛም ከእናንተ ጋር አብረን ስለምንነግሥ መንገሣችሁ መልካም በሆነ ነበር፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች