Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 21:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 በፊታቸው ጠባዩን ለወጠ፤ ከእነርሱ ጋር እያለም ራሱን እብድ አስመሰለ፤ በበሩ መዝጊያ ላይ ቧጠጠ፤ ለሐጩንም በጺሙ ላይ እንዲዝረከረክ አደረገ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ስለዚህ በፊታቸው አእምሮውን እንደ ሳተ ሰው ሆነ፤ በያዙትም ጊዜ የከተማዪቱን ቅጥሮች እየቦጫጨረ፣ ልጋጉንም በጢሙ ላይ እያዝረበረበ እንደ እብድ ሆነ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ስለዚህ በፊታቸው አእምሮውን እንደሳተ ሰው ሆነ፤ በያዙትም ጊዜ የከተማዪቱን ቅጥሮች እየቦጫጨረ፥ ለሐጩንም በጢሙ ላይ እያዝረከረከ እንደ እብድ ሆነ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 በፊ​ቱም መል​ኩን ለወጠ፤ በዚ​ያ​ችም ቀን አመ​ለጠ። በከ​ተ​ማ​ውም በር ከበሮ ይዞ በእጁ መታ፤ በበ​ሩም መድ​ረክ ላይ ተን​ፈ​ራ​ፈረ፤ ልጋ​ጉም በጢሙ ላይ ይወ​ርድ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 በፊታቸውም አእምሮውን ለወጠ፥ በያዙትም ጊዜ እንደ እብድ ሆነ፥ በበሩም መድረክ ላይ ተንፈራፈረ፥ ልጋጉም በጢሙ ላይ ይወርድ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 21:13
7 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሰውን የሚፈራ ችግር ላይ ይወድቃል፤ በእግዚአብሔር የሚታመን ግን በሰላም ይኖራል።


ግፍን መፈጸም ጥበበኛን ሰው እንደ ሞኝ ያደርገዋል፤ ጉቦ መቀበልም መልካም ጠባይን ያበላሻል።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “የማጽናናችሁ እኔ ራሴ ነኝ፤ ታዲያ እንደ ሣር የሚጠወልገውንና መሞት ያለበትን ሰውን የምትፈሩት ለምንድን ነው?


“አንድ ወንድ ወይም አንዲት ሴት በራስ ወይም በአገጭ ላይ ቊስል ቢወጣበት ወይም ቢወጣባት፥


ሳኦልና ወታደሮቹም የፍልስጥኤማዊውን ቃል በሰሙ ጊዜ በፍርሃት ተንቀጠቀጡ።


አኪሽም ባለሟሎቹ ለሆኑት ባለሥልጣኖች “እነሆ! ይህ ሰው እብድ ነው! ታዲያ፥ ስለምን ወደ እኔ አመጣችሁት?


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች