Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 21:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 በፊ​ቱም መል​ኩን ለወጠ፤ በዚ​ያ​ችም ቀን አመ​ለጠ። በከ​ተ​ማ​ውም በር ከበሮ ይዞ በእጁ መታ፤ በበ​ሩም መድ​ረክ ላይ ተን​ፈ​ራ​ፈረ፤ ልጋ​ጉም በጢሙ ላይ ይወ​ርድ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ስለዚህ በፊታቸው አእምሮውን እንደ ሳተ ሰው ሆነ፤ በያዙትም ጊዜ የከተማዪቱን ቅጥሮች እየቦጫጨረ፣ ልጋጉንም በጢሙ ላይ እያዝረበረበ እንደ እብድ ሆነ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ስለዚህ በፊታቸው አእምሮውን እንደሳተ ሰው ሆነ፤ በያዙትም ጊዜ የከተማዪቱን ቅጥሮች እየቦጫጨረ፥ ለሐጩንም በጢሙ ላይ እያዝረከረከ እንደ እብድ ሆነ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 በፊታቸው ጠባዩን ለወጠ፤ ከእነርሱ ጋር እያለም ራሱን እብድ አስመሰለ፤ በበሩ መዝጊያ ላይ ቧጠጠ፤ ለሐጩንም በጺሙ ላይ እንዲዝረከረክ አደረገ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 በፊታቸውም አእምሮውን ለወጠ፥ በያዙትም ጊዜ እንደ እብድ ሆነ፥ በበሩም መድረክ ላይ ተንፈራፈረ፥ ልጋጉም በጢሙ ላይ ይወርድ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 21:13
7 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ግፍ ጠቢ​ብን ያሳ​ብ​ደ​ዋል፥ የል​ቡ​ንም ትዕ​ግ​ሥት ያጠ​ፋ​ዋል።


እኔ ነኝ፤ የማ​ጽ​ና​ናሽ እኔ ነኝ፤ አንቺ እን​ግ​ዲህ ዕወቂ፤ ማንን ፈራሽ? የሚ​ሞ​ተ​ውን ሰው እንደ ሣርም የሚ​ጠ​ወ​ል​ገ​ውን የሰው ልጅ ነውን?


“ማና​ቸ​ውም ወንድ ወይም ሴት በራሱ ወይም በአ​ገጩ የለ​ምጽ ደዌ ቢኖ​ር​በት፥ ካህኑ የለ​ም​ጹን ደዌ ያያል፤


ሳኦ​ልና እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ ይህን የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊ​ውን ቃል በሰሙ ጊዜ እጅግ ፈሩ፤ ደነ​ገ​ጡም።


አን​ኩ​ስም ብላ​ቴ​ኖ​ቹን፥ “እነሆ፥ ይህ ሰው እብድ እንደ ሆነ አይ​ታ​ች​ኋል፤ ለምን ወደ እኔ አመ​ጣ​ች​ሁት?


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች