Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 14:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 በኤፍሬም ኮረብታዎች ተደብቀው የነበሩ ሌሎች እስራኤላውያንም ፍልስጥኤማውያን በሽሽት ላይ መሆናቸውን ሰሙ፤ ስለዚህም ከወገን ጦር ጋር ተባብረው ፍልስጥኤማውያንን ማሳደድ ጀመሩ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 በኰረብታማው የኤፍሬም አገር ተሸሽገው የነበሩት እስራኤላውያን ሁሉ ፍልስጥኤማውያኑ በሽሽት ላይ መሆናቸውን በሰሙ ጊዜ፣ አጥብቀው በመከታተል አሳደዷቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 በተራራማው የኤፍሬም አገር ተሸሽገው የነበሩት እስራኤላውያን ሁሉ ፍልስጥኤማውያኑ በሽሽት ላይ መሆናቸውን በሰሙ ጊዜ፥ እነርሱም አጥብቀው በመከታተል ሊወጉአቸው አሳደዷቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 በተ​ራ​ራ​ማ​ውም በኤ​ፍ​ሬም ሀገር የተ​ሸ​ሸ​ጉት እስ​ራ​ኤል ሁሉ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን እንደ ሸሹ በሰሙ ጊዜ እነ​ርሱ ደግሞ ሊዋ​ጉ​አ​ቸው ተከ​ተ​ሉ​አ​ቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 ከእስራኤልም ሰዎች በተራራማው በኤፍሬም አገር የተሸሸጉት ሁሉ ፍልስጥኤማውያን እንደ ኮበለሉ በሰሙ ጊዜ እነርሱ ደግሞ ሊዋጉአቸው ተከትለው ገሠገሡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 14:22
4 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከዚህ በኋላ የንፍታሌም፥ የአሴርና መላው የምናሴ ነገድ ተጠርተው ወጥተው ምድያማውያንን አሳደዱ፤


እስራኤላውያን ሁኔታው አስጊ መሆኑን ባዩና ሠራዊቱም መዋከቡን በተመለከቱ ጊዜ በዋሻ፥ በሾኽ ቊጥቋጦ፥ በአለቶች መካከል በጒድጓዶችና በጒድባ ውስጥ ተሸሸጉ፤


እነርሱም ወጣ ብለው ለፍልስጥኤማውያን ታዩአቸው፤ ፍልስጥኤማውያንም “እነሆ! አንዳንድ ዕብራውያን ከተሸሸጉበት ጒድጓድ በመውጣት ላይ ናቸው!” ተባባሉ፤


ከዮርዳኖስ ወንዝ በስተ ምሥራቅና በኢይዝራኤል ሸለቆ ማዶ የነበሩ እስራኤላውያንም የእስራኤል ሠራዊት መሸሹን፥ ሳኦልና ልጆቹም መገደላቸውን ሰምተው ከተሞቻቸውን እየጣሉ ሸሹ፤ ፍልስጥኤማውያንም መጥተው ከተሞቹን ያዙ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች