Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ምሳሌ 29:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ደምን ለማፍሰስ የሚሹ ሰዎች ንጹሑን ሰው ይጠላሉ፥ እንዲሁም የቅኑን ሰው ነፍስ ይሻሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ደም የተጠሙ ሰዎች ሐቀኛን ሰው ይጠላሉ፤ ቅን የሆነውንም ለመግደል ይሻሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ነፍሰ ገዳዮች ንጹሑን ሰው ይጠላሉ፤ ደጋግ ሰዎችንም ለመግደል ይፈልጋሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ምሳሌ 29:10
24 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሁሉም በእያንዳንዱ በፊቱ የነበረውን ሰው ገደለ፤ ሶርያውያንም ሸሹ፤ እስራኤልም አሳደዱአቸው፥ የሶርያም ንጉሥ የአዴር ልጅ በፈረሱ አመለጠ።


አክዓብም “የይምላ ልጅ የሆነ ሚክያስ የተባለ ሌላ ነቢይም አለ፤ ነገር ግን እኔ እርሱን አልወደውም፤ እርሱ ምንጊዜም ቢሆን ስለ እኔ ክፉ እንጂ መልካም የትንቢት ቃል አይናገርም!” ሲል መለሰለት። ኢዮሣፍጥም “ይህን ማለት አይገባህም!” አለው።


የእስራኤልም ንጉሥ ኢዮሣፍጥን እንዲህ አለው፦ “ጌታን የምንጠይቅበት አንድ ሰው አለ፤ ነገር ግን ሁልጊዜ ስለ እኔ ክፉ እንጂ ከቶ መልካም ትንቢት አይናገርምና እጠላዋለሁ፤ እርሱም የይምላ ልጅ ሚክያስ ነው።” ኢዮሣፍጥም፦ “ንጉሡ እንዲህ አይበል” አለው።


አምላኬ ሆይ፥ ከጠላቶቼ አድነኝ፥ በላዬም ከቆሙት አስጥለኝ።


የተፈጸመች ፈቃድ ሰውነትን ደስ ታሰኛለች፥ ሰነፎች ግን ከክፉ መራቅን ይጸየፋሉ።


ኃጢአተኛ በጻድቃን ዘንድ አስጸያፊ ነው፥ በቀና መንገድ የሚሄደውም በኀጥኣን ዘንድ አስጸያፊ ነው።


ጠቢብ ከሞኝ ጋር ቢጣላ፥ ሞኙ ወይም ይቈጣል ወይም ይስቃል፥ ዕረፍትም አይኖርም።


ለነፍሴ ጉድጓድ ቈፍረዋልና በውኑ በመልካም ፋንታ ክፉ ይመለሳልን? ስለ እነርሱ በመልካም ለመናገር ቁጣህንም ከእነርሱ ለመመለስ በፊትህ እንደ ቆምሁ አስታውስ።


ኤርምያስንም በገመዱ ጐተቱት፤ ከጉድጓድም አወጡት፤ ኤርምያስም በእስር ቤት አደባባይ ተቀመጠ።


በንጉሡም ቤት የነበረው ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ አቤሜሌክ ኤርምያስን በጉድጓዱ ውስጥ እንዳኖሩት ሰማ። ንጉሡም በብንያም በር ተቀምጦ ነበር።


ኢየሱስም “አባት ሆይ! የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው፤” አለ። ልብሱንም ዕጣ ተጣጥለው ተካፈሉት።


እኔ ግን የሰው ምስክር የሚያስፈልገኝ አይደለሁም፤ እናንተ እንድትድኑ ይህን እላለሁ እንጂ።


ተንበርክኮም “ጌታ ሆይ! ይህን ኃጢአት አትቁጠርባቸው፤” ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ። ይህንም ብሎ አንቀላፋ። ሳውልም በእርሱ መገደል ተስማምቶ ነበር።


ወንድሞች ሆይ! የልቤ መልካም ምኞትና እግዚአብሔርንም የምለምነው እስራኤላውያን እንዲድኑ ነው።


“እኔን ከመከተል ተመልሶአልና፥ ትእዛዜንም አልፈጸመምና፥ ሳኦልን በማንገሤ ተጸጽቻለሁ።” ሳሙኤልም እጅግ ተቆጥቶ፥ ሌሊቱን ሁሉ ወደ ጌታ ጮኸ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች