Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘሌዋውያን 25:34 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

34 በከተማቸውም ዙሪያ ያለው መሰማሪያ የዘለዓለም ርስታቸው ነውና አይሸጥም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

34 በከተሞቻቸው ዙሪያ ያለው የግጦሽ መሬት ግን አይሸጥ፤ ለዘላለም ቋሚ ንብረታቸው ነውና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

34 ነገር ግን በሌዋውያን ከተሞች ዙሪያ የሚገኝ የግጦሽ ሣር መሬት ፈጽሞ አይሸጥም፤ እርሱ ለዘለዓለም ቀዋሚ ንብረታቸው ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

34 በከ​ተ​ማ​ዎ​ቻ​ቸው ዙሪያ ያሉ እር​ሻ​ዎ​ቻ​ቸ​ውም የዘ​ለ​ዓ​ለም ርስ​ቶ​ቻ​ቸው ናቸ​ውና አይ​ሸ​ጡም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

34 በከተማቸውም ዙሪያ ያለችው መሰምርያ የዘላለም ርስታቸው ናትና አትሸጥም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘሌዋውያን 25:34
7 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በየከተማይቱም ሁሉ በከተማቸው መሰማሪያዎች ውስጥ ላሉ ለአሮን ልጆች ለካህናቱ፥ ከካህናቱም ወገን ላሉ ወንዶች ሁሉ፥ በትውልዳቸውም ለተቈጠሩ ሌዋውያን ሁሉ ድርሻቸውን እንዲሰጡአቸው በስማቸው የተጻፉ ሰዎች ነበሩ።


ለሌዋውያኑ በካህናቱ ድንበር አጠገብ ርዝመቱ ሀያ አምስት ሺህ ወርዱም ዐሥር ሺህ ይሆናል፥ ርዝመቱ ሁሉ ሀያ አምስት ሺህ ወርዱም ዐሥር ሺህ ክንድ ይሆናል።


ለጌታ የተቀደሰ ስለሆነ ከእርሱ ምንም አይሸጡም አይለውጡም፥ የምድሪቱንም በኵራት ወደ ሌላ አይተላለፍም።


ምድሪቱም የእኔ ናትና፥ እናንተም ከእኔ ዘንድ እንግዶችና መጻተኞች ናችሁና ምድሪቱን ለዘለዓለም አትሽጧት።


ማናቸውም ሰው ከሌዋውያን ቤት ቢገዛ፥ በእስራኤል ልጆች መካከል በሌዋውያን ከተሞች ያሉ ቤቶች ለሌዋውያን ርስቶቻቸው ናቸውና በርስታቸው ከተማ ውስጥ የተሸጠው ቤት በኢዮቤልዩ ይመለሳል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች