ኢዮብ 28:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)4 ሰው ከሚኖርበት ርቀው መውረጃ ይቈፍራሉ በመንገድኞችም ተረስተዋል፥ ከሰዎችም ርቀው እየተንጠለጠሉ ይወዛወዛሉ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም4 የሰው እግር ረግጦት በማያውቅበት ስፍራ፣ ከሰዎች መኖሪያ ርቆ መውረጃ ጕድጓድ ይቈፍራል፤ ሰው በሌለበት ቦታ ይንጠላጠላል፤ ይወዛወዛል። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም4 ሰው ከሚኖርበት ቦታ ርቀው፥ የሰው እግር ረግጦት ወደማያውቅ ስፍራ ይደርሳሉ። እዚያም ጥልቅ ጒድጓድ ይቈፍራሉ፤ በገመድም ላይ እየተንጠለጠሉ፥ ከሰው ተለይተው ብቻቸውን ይሠራሉ። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)4 በአፈር ምክንያት እንደሚከፈል ወንዝ የጽድቅን መንገድ የረሱ በኀጢአታቸው ይደክማሉ። ከሰዎችም መካከል ይለያሉ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)4 ሰው ከሚኖርበት ርቀው መውረጃ ይቈፍራሉ ከሰውም እግር ተረሱ፥ ከሰዎችም ርቀው እየተንጠለጠሉ ይወዛወዛሉ። ምዕራፉን ተመልከት |