ኢዮብ 26:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)14 እነሆ፥ እነኚህ የሥራዎቹ ጫፎች ብቻ ነው፥ ይህም የሰማነው ነገር ምንኛ ጥቂት ነው! የኃይሉንስ ነጐድጓድ ማን ማስተዋል ይችላል?” ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም14 እነዚህ የሥራው ዳር ዳር ናቸው፤ ስለ እርሱ የሰማነው ምንኛ አነስተኛ ነው! የኀይሉንስ ነጐድጓድ ማን ሊያስተውል ይችላል?” ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም14 እነዚህ ሁሉ እግዚአብሔር ከሚሠራቸው ነገሮች ጥቂቶቹ ናቸው፤ የምንሰማውም ሹክሹክታውን ብቻ ነው፤ የኀይሉን ነጐድጓድማ ማን ሊያስተውል ይችላል?” ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)14 እነሆ ይህ የመንገዱ ክፍል ነው፤ የቀሩትንም ነገሮቹን እንሰማለን፤ በሚያደርግበትስ ጊዜ የነጐድጓዱን ኀይል የሚያውቅ ማን ነው?” ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)14 እነሆ፥ ይህ የመንገዱ ዳርቻ ብቻ ነው፥ ይህም የሰማነው ነገር ምንኛ ጥቂት ነው! የኃይሉንስ ነጐድጓድ ያስተውል ዘንድ ማን ይችላል? ምዕራፉን ተመልከት |