Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኢዮብ 22:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 በጥም የደከመውን ውኃ አላጠጣህም፥ የተራበውንም እንጀራ ከልክለሃል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 የዛሉትን ውሃ አላጠጣህም፤ የተራቡትንም ምግብ ከልክለሃል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ተርበውና ተጠምተው ለደከሙ እህልና ውሃ ከልክለሃል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 ለተ​ጠማ ውኃ አላ​ጠ​ጣ​ህም፥ የራ​ብ​ተ​ኛ​ው​ንም ጕርሻ ነጥ​ቀ​ሃል፥ ምድ​ርን የሚ​ዘራ ሰውም በው​ስጧ ድን​በ​ርን ያኖ​ራል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 ለደካማ ውኃ አላጠጣህም፥ ለራብተኛም እንጀራን ከልክለሃል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢዮብ 22:7
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

“ድሀውን ከሚያስፈልገው ከልክዬ፥ የመበለቲቱን ዐይን አጨልሜ እንደሆነ፥


እንጀራዬን ለብቻዬ በልቼ እንደሆነ፥ ወላጅ አልባውም ሳይደርሰው ቀርቶ እንደሆነ፥


በድንኳኔ ሥር የሚኖሩ ሰዎች፦ ‘በሥጋ ያልጠገበ ማን ይገኛል?’ ይሉ የለምን?


በተነ፥ ለችግረኞችም ሰጠ፥ ጽድቁ ለዘለዓለም ዓለም ይኖራል፥ ቀንዱም በክብር ከፍ ከፍ ይላል።


ለድሀ ቸርነትን የሚያደርግ ለጌታ ያበድራል፥ በጎነቱንም መልሶ ይከፍለዋል።


ነፍስህንም ለተራበ ብታፈስስ፥ የተጨነቀውንም ነፍስ ብታጠግብ፥ ብርሃንህ በጨለማ ይወጣል ጨለማህም እንደ ቀትር ይሆናል።


እንጀራህንስ ለተራበ እንድትቈርስ፥ ስደተኞቹን ድሆች ወደ ቤትህ እንድታስገባ፥ የተራቈተውን ብታይ እንድታለብሰው፥ ከሥጋ ዘመድህ እንዳትሸሽግ አይደለምን?


ሰውን ባያስጨንቅ፥ መያዣውን ባይወስድ፥ ባይቀማ፥ ከምግቡ ለተራበ ቢሰጥ፥ የተራቆተውንም በልብስ ቢሸፍን፥


ማንንም ሰው ባያስጨንቅ፥ ነገር ግን ለባለ ዕዳው መያዣውን ቢመልስ፥ ባይቀማ፥ ከምግቡ ለተራበ ቢሰጥ፥ የተራቆተውንም በልብስ ቢሸፍን፥


ተርቤ አላበላችሁኝምና፤ ተጠምቼ አላጠጣችሁኝም፤


ነገር ግን ጠላትህ ቢርበው አብላው፤ ቢጠማው አጠጣው፤ ይህን በማድረግህ በራሱ ላይ የእሳት ፍም ትከምራለህና።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች