ኤርምያስ 25:30 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)30 ስለዚህ እነዚህን ሁሉ ቃላት በእነርሱ ላይ ትንቢት ትናገራለህ፥ እንዲህም ትላቸዋለህ፦ ጌታ በላይ ሆኖ ይጮኻል፥ በቅዱስ ማደሪያውም ሆኖ ድምፁን ያሰማል፤ በበረቱ ላይ እጅግ ይጮኻል፥ ወይንም እንደሚጠምቁ በምድር በሚኖሩ ሁሉ ላይ ይጮኻል። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም30 “እንግዲህ ይህን ቃል ሁሉ ትንቢት ተናገርባቸው፤ እንዲህም በላቸው፣ “ ‘እግዚአብሔር ከላይ ይጮኻል፤ ከቅዱስ ማደሪያው ነጐድጓዳማ ድምፁን ያሰማል፤ በራሱ ምድር ላይ እጅግ ይጮኻል፤ እንደ ወይን ጨማቂዎች፣ በምድር በሚኖሩት ሁሉ ላይም ያስገመግማል፤ ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም30 “ኤርምያስ ሆይ! አንተም እኔ የነገርኩህን ቃል ሁሉ ማወጅ አለብህ፤ እነዚህን ሕዝቦች እንዲህ በላቸው፦ ‘እግዚአብሔር ከሰማይ ከፍተኛ ድምፅ ያሰማል፤ ከቅዱስ መኖሪያውም ነጐድጓድ ያሰማል፤ በምድሩም ላይ ከፍተኛ ድምፅ ያሰማል፤ ወይን እንደሚጨምቁ በከፍተኛ ድምፅ ይናገራል፤ በምድር በሚኖሩ ሁሉ ላይ ከፍተኛ ድምፅ ያሰማል። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)30 “ስለዚህም ይህን ቃል ሁሉ ትንቢት ትናገርባቸዋለህ፤ እንዲህም ትላቸዋለህ፦ እግዚአብሔር በላይ ሆኖ እንደ አንበሳ ያገሣል፤ በቅዱስ ማደሪያውም ሆኖ ድምፁን ያሰማል፤ በበረቱ ላይ እጅግ ያገሣል፤ ወይንም እንደሚጠምቁ በምድር በሚኖሩ ሁሉ ላይ ይጮኻል። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)30 ስለዚህ ይህን ቃል ሁሉ ትንቢት ትናገርባቸዋለህ፥ እንዲህም ትላቸዋለህ፦ እግዚአብሔር በላይ ሆኖ ይጮኻል፥ በቅዱስ ማደሪያውም ሆኖ ድምፁን ያሰማል፥ በበረቱ ላይ እጅግ ይጮኻል፥ ወይንም እንደሚጠምቁ በምድር በሚኖሩ ሁሉ ላይ ይጮኻል። ምዕራፉን ተመልከት |