Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኢሳይያስ 55:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ከአፌ የሚወጣ ቃል እንዲሁ ይሆናል፤ የምሻውን ያደርጋል፤ የላክሁትንም ይፈጽማል እንጂ ወደ እኔ በከንቱ አይመለስም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ከአፌ የሚወጣውም ቃሌ፣ በከንቱ ወደ እኔ አይመለስም፤ ነገር ግን የምሻውን ያከናውናል፤ የተላከበትንም ዐላማ ይፈጽማል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ከእኔ አንደበት የሚወጣውም ቃል እንደዚሁ ነው። እርሱ የላክሁትን ጉዳይ ሳያከናውንና ተልእኮውን ሳይፈጽም ወደ እኔ አይመለስም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ከአፌ የሚ​ወጣ ቃሌ እን​ዲሁ ነው፤ የም​ሻ​ውን እስ​ኪ​ያ​ደ​ርግ ድረስ ወደ እኔ በከ​ንቱ አይ​መ​ለ​ስም፤ መን​ገ​ዴ​ንና ትእ​ዛ​ዜን አከ​ና​ው​ና​ለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ከአፌ የሚወጣ ቃል እንዲሁ ይሆናል፥ የምሻውን ያደርጋል የላክሁትንም ይፈጽማል እንጂ ወደ እኔ በከንቱ አይመለስም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢሳይያስ 55:11
29 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሣሩ ይደርቃል አበባውም ይረግፋል፥ የአምላካችን ቃል ግን ለዘለዓለም ጸንታ ትኖራለች።


ቃሌ ከአፌ በጽድቅ ወጥታለች፥ አትመለስም፦ ጉልበት ሁሉ ለእኔ ይንበረከካል፥ ምላስም ሁሉ በእኔ ይምላል ብዬ በራሴ ምያለሁ።


በመጀመሪያ መጨረሻውን፥ ከጥንትም ያልተደረገውን እነግራለሁ፤ “ምክሬ ትጸናለች ፈቃዴንም ሁሉ እፈጽማለሁ” እላለሁ።


ጌታም በደዌ ያደቅቀው ዘንድ ፈቀደ፤ ነፍሱን ስለ ኃጢአት መሥዋዕት ካደረገ በኋላ ዘሩን ያያል፥ ዕድሜውም ይረዝማል፥ የጌታም ፈቃድ በእጁ ይከናወናል።


ይህ ለኔ እንደ ኖኅ ውኃ ነው፤ የኖኅ ውኃ ደግሞ በምድር ላይ እንዳያልፍ እንደ ማልሁ፥ እንዲሁ አንቺን እንዳልቈጣ እንዳልዘልፍሽም ምያለሁ።


ከእነርሱ ጋር ያለው ቃል ኪዳኔ ይህ ነው ይላል ጌታ፤ በአንተ ላይ ያለው መንፈሴ በአፍህም ውስጥ ያደረግሁት ቃሌ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘለዓለም ድረስ ከአፍህ፥ ከዘርህም አፍ፥ ከዘር ዘርህም አፍ አይለይም፥ ይላል ጌታ።


ደግሞ የጌታ ቃል፦ “ኤርምያስ ሆይ! ምን ታያለህ?” እያለ ወደ እኔ መጣ። እኔም “የለውዝ በትር አያለሁ” አልኩት።


ጌታም “ቃሌን ልፈጽመው ነቅቼ እየጠበቅሁ ነኝና መልካም አይተሃል” አለኝ።


ሁለተኛም ጊዜ የጌታ ቃል “ምን ታያለህ?” ሲል ወደ እኔ መጣ። እኔም “የሚፈላ የሸክላ ድስት ከሰሜን ፊቱን አዘንብሎ አያለሁ” አልሁ።


የጌታ ቁጣ የልቡን አሳብ ሠርቶ እስኪፈጽም ድረስ አይመለስም፤ በኋለኛው ዘመን ፈጽማችሁ ታስተውሉታላችሁ።


በእርሷም ላይ የተናገርሁትን ቃሎቼን ሁሉ፥ ማለት ኤርምያስ በአሕዛብ ሁሉ ላይ ትንቢት የተናገረውን በዚህች መጽሐፍ የተጻፈውን ሁሉ፥ በዚያች ምድር አመጣለሁ።


እኔ ጌታ ተናግሬአለሁ፤ ይፈፀማል፥ እኔም አደርገዋለሁ፤ አልቆጠብም፥ አልራራም፥ አልጸጸትም። እንደ መንገድሽና እንደ ሥራሽ ይፈርዱብሻል፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።


እነሆም፥ ጌታ ያዝዛል፤ ታላቁንም ቤት በማፍረስ፥ ታናሹንም ቤት በመሰባበር ይመታል።


ነገር ግን ለአገልጋዮቼ ለነቢያት ያዘዝኳቸው ቃሎቼና ሥርዓቴ በአባቶቻችሁ ላይ አልደረሱምን? ከዚያ እነርሱም ተጸጽተው፦ “የሠራዊት ጌታ በመንገዳችንና በሥራችን መጠን ሊያደርግብን ያሰበውን እንዲሁ አድርጎብናል” በማለት ተቀበሉ።


ሐሰትን ይናገር ዘንድ እግዚአብሔር ሰው አይደለም፥ ይጸጸትም ዘንድ የሰው ልጅ አይደለም። እርሱ ያለውን አያደርገውምን? የተናገረውንስ አይፈጽመውምን?


ሰማይና ምድር ያልፋሉ፤ ቃሌ ግን አያልፍም።


ሕይወትን የሚሰጥ መንፈስ ነው፤ ሥጋስ ምንም አይጠቅምም፤ እኔ የነገርኋችሁ ቃል መንፈስ ነው፤ ሕይወትም ነው።


ስለዚህ እምነት የሚመጣው ከመስማት ነው፤ መስማትም በክርስቶስ ቃል በኩል ነው።


የመስቀሉ መልዕክት ለሚጠፉት ሞኝነት፥ ለእኛ ለምንድን ግን የእግዚአብሔር ኃይል ነው።


ትምህርቴ እንደ ዝናብ ይዝነብ፤ ንግግሬ እንደ ጠል ይንጠባጠብ፤ በልምላሜ ላይ እንደ ጤዛ፥ በሣርም ላይ እንደ ካፊያ፥ በቡቃያም ላይ እንደሚወርድ ዝናብ፥


ስለዚህም የመልእክትን ቃል፥ እርሱም የእግዚአብሔርን ቃል ከእኛ በተቀበላችሁ ጊዜ፥ በእውነት እንዳለ በእናንተ በአማኞች ደግሞ እንደሚሠራ እንደ እግዚአብሔር ቃል እንጂ እንደ ሰው ቃል አድርጋችሁ ስላልተቀበላችሁት፥ እኛ ደግሞ እግዚአብሔርን ሳናቋርጥ እናመሰግናለን።


ብዙ ጊዜ በእርስዋ ላይ የሚወርደውን ዝናብ የምትጠጣ መሬት፥ ለሚያርሱአትም ደግሞ የምትጠቅምን አትክልት የምታበቅል፥ ከእግዚአብሔር በረከትን ታገኛለችና፤


ለፍጥረቱ የበኵራት እንድንሆን በገዛ ፈቃዱ በእውነት ቃል ወለደን።


ዳግመኛ የተወለዳችሁት በሕያውና ጸንቶ በሚኖር በእግዚአብሔር ቃል አማካይነት ከማይጠፋ ዘር እንጂ፤ ከሚጠፋ ዘር አይደለም።


ሳሙኤል አደገ፤ ጌታም ከእርሱ ጋር ነበረና፥ ከሚናገረው ቃል አንዳች በምድር አይወድቅም ነበር።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች