Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኢሳይያስ 40:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 እንግዲህ የሚስተካከለኝ ማን አለ? ከማንስ ጋር አመሳሰላችሁኝ? ይላል ቅዱሱ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 ቅዱሱ፣ “ከማን ጋራ ታወዳድሩኛላችሁ? የሚስተካከለኝስ ማን አለ?” ይላል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 “ታዲያ፥ እኔን ከማን ጋር ታነጻጽሩኛላችሁ? ከማንስ ጋር ታመሳስሉኛላችሁ?” ይላል ቅዱስ እግዚአብሔር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 እን​ግ​ዲህ እተ​ካ​ከ​ለው ዘንድ በማን መሰ​ላ​ች​ሁኝ? ይላል ቅዱሱ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 እንግዲህ እተካከላለው ዘንድ በማን መሰላችሁኝ? ይላል ቅዱሱ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢሳይያስ 40:25
8 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አቤቱ፥ ከአማልክት የሚመስልህ የለም፥ ሥራህንም የሚመስል የለም።


ጌታን በደመናት የሚተካከለው ማን ነው? ከአማልክትስ ልጆች ጌታን ማን ይመስለዋል?


ከአማልክት መካከል ጌታ ሆይ፥ እንደ አንተ ያለ ማን ነው? በቅድስና ባለግርማ፥ በምስጋና የተፈራህ፥ ድንቅንም የምታደርግ፥ እንደ አንተ ያለ ማን ነው?


እንግዲህ እግዚአብሔርን በማን ትመስሉታላችሁ? ወይስ በምን ምሳሌ ታስተያዩታላችሁ?


በማን ትመስሉኛላችሁ? ከማንስ ጋር ታስተካክሉኛላችሁ? እንመሳሰል ዘንድ ከማን ጋር ታስተያዩኛላችሁ?


እናንተን ከእሳት ውስጥ ሆኖ እንደ ተናገረው፥ የእግዚአብሔርን ድምፅ ሰምቶ በሕይወት መኖር የቻለ፥ ሌላ ሕዝብ ከቶ አለን?


“ ‘በላይ በሰማይ ካለው፥ በታችም በምድር ካለው፥ ከምድርም በታች በውኃ ካለው ነገር የማናቸውንም ምሳሌ የተቀረጸውንም ምስል ለአንተ አታድርግ፥


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች