ኢሳይያስ 28:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)4 በለምለሙ ሸለቆ ራስ ላይ ያለች የረገፈች የክብሩ ጌጥ አበባ ከመከር በፊት አስቀድማ እንደምትበስል በለስ ትሆናለች፤ያያት ሁሉ እጁን ሰዶ ይበላታል። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም4 በለምለሙ ሸለቆ ዐናት ላይ ጕብ ብላ፣ የክብሩ ውበት የሆነች ጠውላጋ አበባ፣ ከመከር በፊት እንደ ደረሰች፣ ሰውም ድንገት አይቶ እንደሚቀጥፋት ወዲያውኑም እንደሚውጣት በለስ ትሆናለች። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም4 ከለምለሙ ሸለቆ በላይ ያለችው ሰማርያ በፍጥነት ክብርዋን ታጣለች፤ እርስዋም እንደሚረግፍ አበባና በበለስ ወራት መጀመሪያ በስለው በመገኘታቸው ተለቅመው እንደሚበሉ የበለስ ፍሬዎች ትሆናለች። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)4 በረዥም ተራራ ራስ ላይ ያለች የረገፈች የክብሩ ተስፋ አበባ አስቀድማ እንደምትበስል በለስ ትሆናለች፤ ሰውም ባያት ጊዜ በእጁ ሳይቀበላት ይበላት ዘንድ ይፈጥናል። ምዕራፉን ተመልከት |