ኢሳይያስ 14:30 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)30 የድሆችም የበኩር ልጆች ይሰማራሉ፥ ችግረኞችም ተዘልለው ይተኛሉ፤ ሥርህንም በራብ እገድላለሁ፥ ቅሬታህም ይገደላል። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም30 ከድኻም ድኻ የሆኑት መሰማሪያ ያገኛሉ፤ ችግረኞችም ያለ ሥጋት ይተኛሉ፤ ሥርህን ግን በራብ እገድላለሁ፤ ትሩፋንህንም እፈጃለሁ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም30 እጅግ የደኸዩ መጠጊያ ያገኛሉ፤ ድኽነት ያጠቃቸውም ተዝናንተው ይኖራሉ፤ የእናንተን ልጆች ግን በራብ እገድላለሁ፤ የተረፋችሁትንም አጠፋለሁ። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)30 ድሆችም በውስጣችሁ ይሰማራሉ፤ ድሆች ሰዎችም በሰላም ያርፋሉ፤ ዘራችሁንም ረኃብ ያጠፋቸዋል፤ ከእናንተም የቀሩት ያልቃሉ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)30 የድሆችም የበኵር ልጆች ይሰማራሉ፥ ችግረኞችም ተዘልለው ይተኛሉ፥ ሥርህንም በራብ እገድላለሁ፥ ቅሬታህም ይገደላል። ምዕራፉን ተመልከት |