ዘፀአት 36:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)19 ለድንኳኑ መሸፈኛ ከቀይ አውራ በግ ቁርበት፥ በላዩ ላይ የሚሆን መሸፈኛ ከአቆስጣ ቁርበት ሠራስስ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም19 ከዚያም ለድንኳኑ መሸፈኛ የሚሆን ቀይ ከተነከረ የአውራ በግ ቈዳ ሠሩ፤ በላዩ ላይ የሚሆንም የአቆስጣ ቈዳ አበጁ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም19 ከውጪ በኩል መክደኛ ይሆኑ ዘንድ አንደኛውን ቀይ ቀለም ከተነከረ የአውራ በግ ቆዳ፥ ሌላውንም ከለፋ ቊርበት ሌሎች ሁለት መጋረጃዎችን ሠሩ። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)19 ለድንኳኑም መደረቢያ ከቀይ አውራ በግ የተለፋ ቍርበት፥ ከዚያም በላይ ሌላ መደረቢያ ከአቆስጣ ቍርበት አደረጉ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)19 ለድንኳኑም መደረቢያ ከቀይ ከአውራ በግ ቁርበት፥ ከዚያም በላይ ሌላ መደረቢያ ከአቆስጣ ቁርበት አደረጉ። ምዕራፉን ተመልከት |