ዘፀአት 34:34 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)34 ሙሴ ከእርሱ ጋር ለመነጋገር ወደ ጌታ በገባ ጊዜ፥ እስኪ ወጣ ድረስ መሸፈኛውን አነሣ፤ በወጣም ጊዜ ለእስራኤል ልጆች የታዘዘውን ነገር ነገራቸው። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም34 ሙሴም ከርሱ ጋራ ለመነጋገር ወደ እግዚአብሔር ሀልዎት በሚገባበት ጊዜ ሁሉ ግን፣ እስከሚወጣ ድረስ መሸፈኛውን ያነሣ ነበር፤ በወጣም ጊዜ የታዘዘውን ለእስራኤላውያን ነገራቸው። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም34 ሙሴ ከእግዚአብሔር ጋር ለመነጋገር ወደ እግዚአብሔር መገኛ ድንኳን በገባ ቊጥር ሻሹን ከፊቱ ላይ ያነሣ ነበር፤ ከዚያም በሚወጣበት ጊዜ የታዘዘውን ሁሉ ለእስራኤላውያን ይነግራቸው ነበር። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)34 ሙሴም ከእርሱ ጋር ይነጋገር ዘንድ ወደ እግዚአብሔር በገባ ጊዜ እስኪወጣ ድረስ መሸፈኛውን ከፊቱ ያነሣ ነበር፤ በወጣም ጊዜ ለእስራኤል ልጆች የታዘዘውን ነገር ይነግራቸው ነበር። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)34 ሙሴም ከእርሱ ጋር ሲነጋገር ወደ እግዚአብሔር በገባ ጊዜ እስኪ ወጣ ድረስ መሸፈኛውን ከፊቱ አነሣ፤ በወጣም ጊዜ ለእስራኤል ልጆች የታዘዘውን ነገር ነገረ። ምዕራፉን ተመልከት |