ዘዳግም 31:28 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)28 ይህን ቃል በጆሮአቸው እናገር ዘንድ፥ ሰማይንና ምድርንም አስመሰክርባቸው ዘንድ የነገዶቻችሁን ሽማግሌዎች ሁሉ አለቆቻችሁንም ሰብስቡልኝ፥ ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም28 ይህን ቃል ይሰሙ ዘንድ እንድናገር፣ ሰማይንና ምድርን ምስክር አድርጌ እንድጠራባቸው፣ የነገድ አለቆቻችሁን በሙሉና ሹሞቻችሁን ሁሉ በፊቴ ሰብስቡ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም28 ስለዚህም ይህን ሁሉ እነግራቸው ዘንድ የነገድ መሪዎቻችሁንና የሕዝብ አለቆችን ሰብስቡልኝ፤ እኔ ሰማይንና ምድርን በእነርሱ ላይ ምስክሮች አድርጌ እጠራለሁ። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)28 ይህን ቃል በጆሮአቸው እነግር ዘንድ፥ ሰማይንና ምድርንም አስመሰክርባቸው ዘንድ የነገዶቻችሁን አለቆች፥ ሽማግሌዎቻችሁን ሁሉ፥ ሹሞቻችሁንም፥ ጻፎቻችሁንም ሰብስቡልኝ፤ ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)28 ይህን ቃል በጆሮአቸው እናገር ዘንድ፥ ሰማይንና ምድርንም አስመሰክርባቸው ዘንድ የነገዶቻችሁን ሽማግሌዎች ሁሉ አለቆቻችሁንም ሰብስቡልኝ፤ ምዕራፉን ተመልከት |