Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




2 ተሰሎንቄ 3:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 እናንተ ግን ወንድሞች ሆይ! መልካም ሥራን ለመሥራት አትታክቱ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 እናንተ ግን ወንድሞች ሆይ፤ መልካም ሥራን ከመሥራት ከቶ አትታክቱ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 እናንተ ግን ወንድሞች ሆይ! ደከምን ብላችሁ መልካም ከመሥራት አትቦዝኑ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 እናንተ ግን ወንድሞች ሆይ! መልካም ሥራን ለመሥራት አትታክቱ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 እናንተ ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ መልካም ሥራን ለመሥራት አትታክቱ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ተሰሎንቄ 3:13
17 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የጌታን ቸርነት በሕያዋን ምድር እንደማይ አምናለሁ።


በዚያን ቀን ኢየሩሳሌም እንዲህ ይባልላታል፦ “ጽዮን ሆይ፥ አትፍሪ፥ እጆችሽም አይዛሉ።


“እነሆ፥ ይህ ድካም ነው ብላችሁ ጢቅ አላችሁበት፥” ይላል የሠራዊት ጌታ፤ “የተሰረቀውን፥ አንካሳውንና የታመመውን አምጥታችኋል፤ እንዲሁም ቁርባንን አምጥታችኋል፤ በውኑ ከእጃችሁ መቀበል ይገባኛልን?” ይላል ጌታ።


ሳይታክቱም ዘወትር ሊጸልዩ እንደሚገባቸው የሚያስተምር ምሳሌን ነገራቸው፤


በመልካም ሥራ በመጽናት ምስጋናንና ክብርን የማይጠፋንም ሕይወት ለሚፈልጉ የዘለዓለምን ሕይወት ይሰጣቸዋል፤


ሁሉ ከተገዛለት በኋላ እግዚአብሔር ሁሉ በሁሉ እንዲሆን ወልድ ራሱ ደግሞ ሁሉን ላስገዛለት ለእርሱ ይገዛል።


ስለዚህ ይህ አገልግሎት የተሰጠን በእግዚአብሔር ምሕረት ምክንያት ስለሆነ፥ መቼም አንታክትም።


ስለዚህ አንታክትም፤ ውጫዊው ሰውነታችን እየመነመነ ቢሄድ እንኳን፥ ውስጣዊው ሰውነታችን በየዕለቱ ይታደሳል።


“ከዚያም አለቆቹ፥ ‘የሚፈራ ወይም ልቡ የሚባባ ሰው አለን? የወንድሞቹም ልብ እንዳይባባ ወደ ቤቱ ይመለስ’ በማለት ጨምረው ይናገሩ።


ፍቅራችሁ በእውቀትና በማስተዋል ሁሉ ከፊት ይልቅ እያደገ እንዲበዛ እጸልያለሁ፤


እንግዲህ በቀረውስ ወንድሞች ሆይ! እግዚአብሔርን ለማስደሰት እንዴት መመላለስ እንደሚገባችሁ ከእኛ ዘንድ ተቀብላችኋል፤ በእርግጥም እየተመላለሳችሁ ነው፤ ከዚህም በበለጠ አብዝታችሁ እንድታደርጉት በጌታ በኢየሱስ እንለምናችኋለን፤ እንመክራችኋለንም።


ነገር ግን እንደ ወንድም ገሥጹት እንጂ እንደ ጠላት አትቁጠሩት።


በነፍሳችሁ ዝላችሁ እንዳትደክሙ፥ ከኀጢአተኞች የደረሰበትን እንዲህ ያለውን ተቃውሞ እንዴት እንደተቋቋመ አስቡ።


እንደ ልጆችም እንዲህ በማለት የተነገራችሁን ምክር ረስታችኋል፦ “ልጄ ሆይ! የጌታን ተግሣጽ አታቅልል፤ በሚገሥጽህም ጊዜ ተስፋ አትቁረጥ፤


በትዕግስት መጽናትህንና ስለ ስሜ መከራ መቀበልህን አውቃለሁ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች