Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




2 ዜና መዋዕል 8:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 እነዚህም በሕዝቡ ላይ ሥልጣን የነበራቸው የንጉሥ ሰሎሞን ከፍተኛ ሹማምት ሁለት መቶ ኀምሳ ነበሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ከእነዚህም ሁለት መቶ ዐምሳዎቹ የንጉሥ ሰሎሞን ሹማምት ሰዎቹን የሚቈጣጠሩ ነበሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ሰሎሞን ለሚያከናውነው ልዩ ልዩ የሕንጻ ሥራ፥ የጒልበት ሥራ ይሠሩ ዘንድ ለተመደቡት ገባሮች ሁለት መቶ ኀምሳ እስራኤላውያን ኀላፊዎች ነበሩአቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 እነ​ዚ​ህም በሕ​ዝቡ ላይ ያለ​ውን ሥራ የሚ​ቈ​ጣ​ጠሩ የን​ጉሡ የሰ​ሎ​ሞን ዓይ​ነ​ተ​ኞች አለ​ቆች ሁለት መቶ አምሳ ነበሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 እነዚህም በሕዝቡ ላይ ሠልጥነው የነበሩ የንጉሡ የሰሎሞን ዓይነተኞች አለቆች ሁለት መቶ አምሳ ነበሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ዜና መዋዕል 8:10
5 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የእነዚህ ሠራተኞች የበላይ ሆነው ሥራውን የሚቆጣጠሩ ሦስት ሺህ ሦስት መቶ ሰዎችን አዘጋጀ።


ሰሎሞን ለሚያከናውነው የሕንጻ ሥራ የጉልበት ሥራ ይሠሩ ዘንድ ለተመደቡት ሰዎች አምስት መቶ ኀምሳ ኀላፊዎች ነበሩአቸው።


ከእነርሱም የሚሸከሙትን ሰባ ሺህ፥ በተራሮችም ላይ የሚጠርቡትን ሰማንያ ሺህ፥ የሕዝቡንም ሥራ ለሚቆጣጠር የተሾሙትን ሦስት ሺህ ስድስት መቶ ሰዎችን ሾመ።


ሰሎሞንም፦ “የጌታ ታቦት የገባበት ስፍራ ቅዱስ ነውና ሚስቴ በእስራኤል ንጉሥ በዳዊት ቤት አትቀመጥም” ሲል የፈርዖንን ልጅ ከዳዊት ከተማ አውጥቶ ወደ ሠራላት ቤት አመጣት።


ሰሎሞንም ለሥራው ከእስራኤል ልጆች ማንንም ባርያ አላደረገም፤ እነርሱ ግን ወታደሮች፥ የሹማምቶችም አለቆች፥ የሰረገሎችና የፈረሰኞች ባልደራሶች ነበሩ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች