2 ዜና መዋዕል 8:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)11 ሰሎሞንም፦ “የጌታ ታቦት የገባበት ስፍራ ቅዱስ ነውና ሚስቴ በእስራኤል ንጉሥ በዳዊት ቤት አትቀመጥም” ሲል የፈርዖንን ልጅ ከዳዊት ከተማ አውጥቶ ወደ ሠራላት ቤት አመጣት። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም11 ሰሎሞንም፣ “የእግዚአብሔር ታቦት የገባበት ቦታ ሁሉ ቅዱስ ስለ ሆነ፣ ሚስቴ በእስራኤል ንጉሥ በዳዊት ቤተ መንግሥት መኖር አይገባትም” በማለት የፈርዖንን ልጅ ከዳዊት ከተማ እርሱ ወደ ሠራላት ቤተ መንግሥት አመጣት። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም11 ሰሎሞን “የእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ታቦት ያለበት ስፍራ ሁሉ ቅዱስ ስለ ሆነ፥ ግብጻዊት ሚስቴ በእስራኤል ንጉሥ በዳዊት ቤተ መንግሥት ውስጥ መኖር አይገባትም” በማለት የግብጽ ንጉሥ ልጅ የሆነችውን ሚስቱን ከዳዊት ከተማ አውጥቶ እርሱ ወዳሠራላት ወደ ሌላ መኖሪያ ቤት ተዘዋውራ እንድትኖር አደረገ። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)11 ሰሎሞንም፥ “የእግዚአብሔር ታቦት የገባችበት ስፍራ ቅዱስ ነውና ሚስቴ በእስራኤል ንጉሥ በዳዊት ቤት አትቀመጥም” ሲል የፈርዖንን ልጅ ከዳዊት ከተማ ወደ ሠራላት ቤት አወጣት። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)11 ሰሎሞንም “የእግዚአብሔር ታቦት የገባበት ስፍራ ቅዱስ ነውና ሚስቴ በእስራኤል ንጉሥ በዳዊት ቤት አትቀመጥም፤” ሲል የፈርዖንን ልጅ ከዳዊት ከተማ ወደ ሠራላት ቤት አወጣት። ምዕራፉን ተመልከት |