2 ዜና መዋዕል 31:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)6 በይሁዳም ከተሞች የሚኖሩ የእስራኤልና የይሁዳም ልጆች የበሬውንና የበጉን አሥራት፥ ለአምላካቸውም ለጌታ የተቀደሰውን አሥራት አመጡ፥ ከምረውም አስቀመጡት። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም6 በይሁዳ ከተሞች ይኖሩ የነበሩት የእስራኤልና የይሁዳ ሰዎችም ከከብቶቻቸው፣ ከበግና ከፍየል መንጎቻቸውና ለአምላካቸው እግዚአብሔር ከለዩአቸው የተቀደሱ ነገሮች ዐሥራት አውጥተው አመጡ፤ ከመሩትም። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም6 በይሁዳ ከተሞች ሰዎችም ሕዝብም ሁሉ ከቀንድ ከብቶቻቸውና ከበጎቻቸው ዐሥራት አውጥተው ሰጡ፤ እንዲሁም ለአምላካቸው ለእግዚአብሔር የተለየ ያደረጉትን ስጦታ አምጥተው ከመሩት፤ ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)6 በይሁዳም ከተሞች የሚኖሩ የእስራኤልና የይሁዳ ልጆች የበሬዉንና የበጉን፥ የፍየሉንም ዐሥራት አመጡ፤ ለአምላካቸው ለእግዚአብሔርም ቀደሱት፤ ከምረውም አኖሩት። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)6 በይሁዳም ከተሞች የሚኖሩ የእስራኤልና የይሁዳም ልጆች የበሬውንና የበጉን አሥራት፥ ለአምላካቸውም ለእግዚአብሔር የተቀደሰውን አሥራት አመጡ፤ ከምረውም አኖሩት። ምዕራፉን ተመልከት |