Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




1 ነገሥት 12:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 “ወንድሞቻችሁ በሆኑት በእስራኤላውያን ላይ አደጋ አትጣሉ፤ ሁላችሁም ወደየቤታችሁ ሂዱ፤ ይህ የሆነውም በእኔ ፈቃድ ነው” ብሎ እንዲነግር አዘዘው። እነርሱም ሁሉ ለጌታ ቃል ታዛዦች በመሆን ወደየቤታቸው ተመልሰው ሄዱ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 ‘እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው፤ ይህ ነገር ከእኔ የሆነ ነውና ወንድሞቻችሁን እስራኤላውያንን ለመውጋት አትውጡ፤ እያንዳንዳችሁ ወደየቤታችሁ ተመለሱ።’ ” ስለዚህ እግዚአብሔር እንዳዘዘው የእግዚአብሔርን ቃል ሰሙ፤ ወደየቤታቸውም ተመለሱ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 “ወንድሞቻችሁ በሆኑት በእስራኤላውያን ላይ አደጋ አትጣሉ፤ ሁላችሁም ወደየቤታችሁ ሂዱ፤ ይህ የሆነው በእኔ ፈቃድ ነው” ብሎ እንዲነግር አዘዘው። እነርሱም ሁሉ ለእግዚአብሔር ቃል ታዛዦች በመሆን ወደየቤታቸው ተመልሰው ሄዱ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ይህ ነገር ከእኔ ዘንድ ነውና አት​ውጡ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ልጆች ወን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ሁን አት​ውጉ፤ እያ​ን​ዳ​ን​ዱም ወደ ቤቱ ይመ​ለስ።” እነ​ር​ሱም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ሰሙ፤ እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ተመ​ል​ሰው ሄዱ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ‘ይህ ነገር ከእኔ ዘንድ ነውና አትውጡ፤ የእስራኤልንም ልጆች ወንድሞቻችሁን አትውጉ፤ እያንዳንዱም ወደ ቤቱ ይመለስ፤’ ብለህ ንገራቸው፤” ሲል መጣ። የእግዚአብሔርንም ቃል ሰሙ፤ እንደ እግዚአብሔርም ቃል ተመልሰው ሄዱ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ነገሥት 12:24
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ላባና ባቱኤልም መለሱ እንዲህም አሉ፦ “ነገሩ ከእግዚአብሔር ዘንድ መጥቷል ክፉም በጎም ልንመልስልህ አንችልም።


ይህም የሆነበት ምክንያት ከሴሎ በመጣው በነቢዩ አኪያ አማካይነት ስለ ናባጥ ልጅ ስለ ኢዮርብዓም ጌታ የተናገረው ቃል እንዲፈጸም ነው፤ ንጉሥ ሮብዓምም የሕዝቡን ሐሳብ ችላ በማለት ሳይቀበል የቀረበትም ምክንያት ጌታ ይህን ለውጥ ለማድረግ ስለ ወሰነ ነው።


የእስራኤል ንጉሥ ኢዮርብዓም በኮረብታማው በኤፍሬም አገር የምትገኘውን የሴኬምን ከተማ ምሽግ አድርጎ በዚያ ለጥቂት ጊዜ ቆየ፤ ከዚያም በመነሣት የፐኑኤልን ከተማ ምሽግ አድርጎ ሠራ፤


በዚህም ዘመን ሁሉ ሮብዓምና ኢዮርብዓም እርስ በርሳቸው በማያቋርጥ ጦርነት ላይ ነበሩ፤


‘ጌታ እንዲህ ይላል፦ ይህ ነገር ከእኔ ዘንድ ነውና አትውጡ፥ ወንድሞቻችሁንም አትውጉ፤ እያንዳንዱም ወደ ቤቱ ይመለስ።’ ” የጌታንም ቃላት ሰሙ፥ ኢዮርብዓምንም ሄደው ከመውጋት ተመለሱ።


አካዝያስም ወደ ኢዮራም በመምጣቱ እዲጠፋ የጌታ ፈቃድ ነበረ፤ በመጣም ጊዜ ከኢዮራም ጋር ጌታ የአክዓብን ቤት እንዲያጠፋ ወደ ቀባው ወደ ናሜሲ ልጅ ወደ ኢዩ ወጣ።


አሜስያስም ከኤፍሬም የመጡትን ሠራዊት ወደ ስፍራቸው እንዲመለሱ ለይቶ አሰናበታቸው፤ ስለዚህም ቁጣቸው በይሁዳ ላይ ጸና፥ ወደ አገራቸውም በጽኑ ቁጣ ተመለሱ።


ለራሳቸው ነገሥታትን አነገሡ፥ ከእኔም ዘንድ አይደለም፤ አለቆችንም ሾሙ፥ እኔም አላወቅሁም፤ ለመጥፊያቸው ከብራቸውና ከወርቃቸው ጣዖታትን ለራሳቸው ሠሩ።


ጌታ በእናንተ መካከል አይደለምና በጠላቶቻችሁ ፊት እንዳትሸነፉ አትውጡ።


በዚያን ጊዜ በእስራኤል ላይ ገዦቹ ፍልስጥኤማውያን ስለ ነበሩ፥ ከፍልስጥአማውያን ጋር ጠብ እንዲፈጠር ጌታ ሆን ብሎ ያደረገው ነገር መሆኑን አባቱና እናቱ አላወቁም ነበር።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች