ከዚህም በኋላ ሄዶ የገንዘቡን እኩሌታ ይወስድ ዘንድ፥ ወደ አባቱም በደኅና ይሄድ ዘንድ፥ የተረፈውን ግን እርሱና ሚስቱ ከሞቱ በኋላ ይወስድ ዘንድ አስማለው።
ከዛ በኋላ የንብረቴን ግማሹን ውሰድና ያለ ምንም ችግር ይዘሃት ወደ አባትህ ቤት ሂድ፤ የቀረውን ግማሽ ደግሞ እኔና ሚስቴ ስንሞት የእናንተ ይሆናል፤ በርታ ልጄ፥ እኔ አባትህ ነኝ፥ ኤድናም እናትህ ናት፥ ከእኀትህ ወላጆች እንደ ሆንን የአንተም ነን፥ በርታ ልጄ።”