Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -

ይህ መፅሐፍ በእግዚአብሔር አልተነፀረም እና የክርስቲያን ካኖን ወይም የአይሁድ ታናክ ክፍል አይደለም። ለታሪክና ለጥናት ዓላማ ብቻ ይታያል። ሙሉ ማብራሪያን ይመልከቱ

መጽ​ሐፈ ጦቢት 8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)


የጋ​ኔኑ ከሣራ መው​ጣት

1 ተመ​ግ​በ​ውም በጨ​ረሱ ጊዜ ጦብ​ያን ወደ እርሷ አገ​ቡት።

2 ወደ እር​ሷም በገባ ጊዜ የሩ​ፋ​ኤ​ልን ነገር አሰበ፤ የዕ​ጣን ዕራሪ ወሰደ፤ ከዚ​ያም ዓሣ ከል​ቡና ከጉ​በቱ ጨምሮ አጤ​ሰው።

3 ሽታ​ውም ያን ጋኔን በሸ​ተ​ተው ጊዜ እስከ ላይ​ኛው ግብፅ አው​ራጃ ድረስ ሸሸ። ያም መል​አክ ጋኔ​ኑን አሰ​ረው።


የጦ​ብያ ጸሎት

4 ሁለ​ቱም በተ​ዘ​ጋ​ባ​ቸው ጊዜ ጦብያ ከአ​ል​ጋው ተነ​ሥቶ፥ “እኅቴ ተነሽ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይቅር ይለን ዘንድ እን​ጸ​ልይ” አላት።

5 ጦብ​ያም እን​ዲህ ይል ጀመረ፥ “አቤቱ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን አም​ላክ አንተ ቡሩክ ነህ፤ ቅዱስ ስም​ህም ይባ​ረክ፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ሙም ይመ​ሰ​ገ​ናል። ሰማ​ያ​ትና የፈ​ጠ​ር​ሃ​ቸው ሁሉ ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ሃል።

6 አንተ አባ​ታ​ችን አዳ​ምን ፈጠ​ር​ኸው፤ ትረ​ዳ​ውና ታሳ​ር​ፈ​ውም ዘንድ ሔዋ​ንን ሰጠ​ኸው፤ ከእ​ነ​ዚ​ያም የሰው ዘር ተወ​ለደ፤ አን​ተም አልህ፦ ‘ሰው ብቻ​ውን ይኖር ዘንድ መል​ካም አይ​ደ​ለ​ምና የሚ​ረ​ዳ​ውን እን​ፍ​ጠ​ር​ለት።’

7 አሁ​ንም ይህ​ቺን እኅ​ቴን የማ​ገ​ባት በሚ​ገባ ነው እንጂ ስለ ዝሙት አይ​ደ​ለ​ምና አቤቱ አብ​ረን ወደ ሽም​ግ​ልና እን​ድ​ን​ደ​ርስ እን​ረ​ዳዳ ዘንድ ለእ​ኔና ለእ​ርሷ ይቅ​ር​ታን ላክ​ልን።”

8 እር​ሷም ከእ​ርሱ ጋር “አሜን” አለች።

9 ሁለ​ቱም በዚ​ያች ሌሊት አብ​ረው አደሩ።

10 ከዚ​ህም በኋላ ራጉ​ኤል ተነ​ሥቶ ሄደ፤ እር​ሱም “ምና​ል​ባት ይሞት ይሆ​ናል” ብሎ መቃ​ብር ቈፈረ።

11 ራጉ​ኤ​ልም ወደ ቤቱ ተመ​ለሰ።

12 ሚስቱ አድ​ና​ንም አላት፥ “ደኅና እንደ ሆነ ታየው ዘንድ አን​ዲት ልጅ ላኪ፤ ሞቶም እንደ ሆነ ማንም ሳያ​ውቅ እን​ቀ​ብ​ረ​ዋ​ለን።”

13 ያቺም ልጅ ሄዳ ደጃ​ፉን ከፈ​ተች፤ ሁለ​ቱም ተኝ​ተው አገ​ኘ​ቻ​ቸው።

14 ተመ​ል​ሳም እርሱ ደኅና እንደ ሆነ ነገ​ረ​ቻ​ቸው።

15 ራጉ​ኤ​ልም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ሰ​ገ​ነው፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “አቤቱ አንተ የተ​መ​ሰ​ገ​ንህ ነህ፤ ንጽ​ሕ​ትና ቅድ​ስት በሆ​ነች ምስ​ጋና ሁሉ የተ​መ​ሰ​ገ​ንህ ነህ። ጻድ​ቃ​ንህ፦ በሠ​ራ​ኸው ሥራ ሁሉ ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ሃል፤ መላ​እ​ክ​ት​ህና የመ​ረ​ጥ​ኻ​ቸ​ውም ሁሉ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ሃል።

16 ደስ አሰ​ኝ​ተ​ኸ​ኛ​ልና አቤቱ አንተ የተ​መ​ሰ​ገ​ንህ ነህ፤ እንደ ጠረ​ጠ​ር​ሁት አል​ተ​ደ​ረ​ገ​ብ​ኝም፤ ነገር ግን እንደ ቸር​ነ​ትህ ብዛት አደ​ረ​ግ​ህ​ልኝ።

17 አንተ ቡሩክ ነህ፤ ሁለ​ቱን ብቸ​ኞች ይቅር ብለ​ሃ​ቸ​ዋ​ልና፥ ዘመ​ና​ቸ​ውን በደ​ኅ​ን​ነ​ትና በደ​ስታ፥ በቸ​ር​ነ​ትህ ይፈ​ጽሙ ዘንድ አቤቱ በጎ​ነ​ትን አድ​ር​ገ​ህ​ላ​ቸ​ዋ​ልና።”

18 ከዚ​ያም በኋላ ራጉ​ኤል ያን መቃ​ብር ይደ​ፍኑ ዘንድ አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹን አዘ​ዛ​ቸው።


የሰ​ርጉ በዓል

19 ከዚ​ህም በኋላ ዐሥራ አራት ቀን በዓል አደ​ረ​ገ​ላ​ቸው።

20 ራጉ​ኤ​ልም የሠ​ርጉ ዐሥራ አራት የበ​ዓል ቀን እስ​ኪ​ፈ​ጸም ድረስ ወጥቶ እን​ዳ​ይ​ሄድ ጦብ​ያን አማ​ለው።

21 ከዚ​ህም በኋላ ሄዶ የገ​ን​ዘ​ቡን እኩ​ሌታ ይወ​ስድ ዘንድ፥ ወደ አባ​ቱም በደ​ኅና ይሄድ ዘንድ፥ የተ​ረ​ፈ​ውን ግን እር​ሱና ሚስቱ ከሞቱ በኋላ ይወ​ስድ ዘንድ አስ​ማ​ለው።

ተከተሉን:



ማስታወቂያዎች