ራጉኤልም የሠርጉ ዐሥራ አራት የበዓል ቀን እስኪፈጸም ድረስ ወጥቶ እንዳይሄድ ጦብያን አማለው።
እስሱም ጦብያን ጠርቶ “እንግዲህ ወዴትም ሳትሄዱ እዚህ እየበላህና እየጠጣህ ዐሥራ አራት ቀን ከእኔ ጋር ትቆያለህ፥ ብዙ መከራ የደረሰባትን ልጄንም ታስደስታታለህ።